ካፍ በቅርቡ በሀገራችን በሚገኙ ስድስት ስታዲየሞቻችን ያደረገውን የብቁነት ግምገማ ተከትሎ፡ ኢትዮጵያ አለምአቀፍ  ውድድርን ልታካሂድ የምትችልባቸው የካፍ ዝቅተኛውን መስፈርት ሊያሟሉ የሚችሉ ስታዲየሞች እንደሌሏት በደብዳቤ ማሳወቁ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም ኢትዮጵያን በካፍ ሻንፒዮንስ ሊግ እና በኮንፌዴሬሽን ካፕ የወከሉት የመቐለ 70 እንድርታ እና የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድኖች በሀገር ቤት የሚያደረጓቸውን ጨዋታዎች በመቐለ እና በባሕር ዳር ስታዲየሞች ለማካሄድ፡ ከዚህ ቀደም ለቻን 2020 የኢትዮጵያን ዝግጅት ለመመልከት የመጣው የካፍ ገምጋሚ ቡድን በሰጠው ግብረ መልስ መሰረት፡ በስታዲየሞቹ ላይ የተወሰኑ ማሻሻያዎችን በማድረግ ስታዲየሞቹ ፈቃድ እንዲያገኙ በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በኩል ጥያቄያቸውን ለካፍ አቅርበዋል፡፡

በመሆኑም ካፍ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያቀረበውን ጥያቄ በመመልከት ስታዲየሞቹ ዝቅተኛውን መስፈርት በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ እንዲያሟሉ እና ኢትዮጵያ የምትሳተፍባቸው የክለቦች እና የብሄራዊ ቡድን ውድድሮችን በመቐለ እና በባህር ዳር ስታዲየሞች ብቻ እንድትጠቀም ከዛሬ ነሃሴ 1 እስከ ጥቅምት 1 ለሁለት ወራት ያህል መፍቀዱን ዛሬ በላከው ደብዳቤ አሳታውቋል፡፡

በነዚህ ሁለት ወራት ጊዜ ውስጥም ስታዲየሞቹ ያላሟሏቸውን ግብዓቶች እንዲያሟሉ እንዲደረግ እና ለሌላ የስታዲየም ግምገማ ፌደሬደሽኑ በድጋሚ እንዲጠይቅ ካፍ አሳስቧል፡፡

መረጃው፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ነው

author image

About Liyusport.com

ልዩ ስፖርት ድረ-ገጽ የኢትዮጵያን ስፖርት እና ከባቢውን በመሰረታዊነት ሊለውጡ የሚችሉ የባለሙያ ሃሳቦች: ትችቶች፡ የምርምር ውጤቶች እና ሀተታዊ ጽሁፎች በራሳቸው በባለሞያወቹ ብዕር እና አንደበት ተዘጋጅተው በጽሁፍ እና በድምጽ የሚስተናገዱበት፡ እንዲሁም የምርመራ ጋዜጠኝነትን ጨምሮ ልዩ ልዩ የጋዜጠኝነት ውጤት የሆኑ ፅሁፎች የሚቀርቡበት እና በአይነቱ ልዩ የሆነ የስፖርት ድረ-ገፅ ነው፡፡

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *