የካፍ የስነ-ስርዓት ኮሚቴ የ2018/19 የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ መጠናቀቅን ተከትሎ፡ ሞሮኳዊዉ ፋውዚ ሌክያ በኢንተርናሽናል ዳኛ ባምላክ ተሰማ ላይ የፈጸሙትን ጥቃት አስመልክቶ ሲያደርገው የነበረውን ምርመራ አጠናቆ ውሳኔውን አሳውቋል፡፡
በዚህም መሰረት “ምንም እንኳን አርቢትር ባምላክ ተሰማ እና የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ግለሰቡ ጥፋት መፈጸማቸውን ገልጸው በጽሁፍ ማመልከቻ ቢያስገቡም፡ በምክትል ሰብሳቢው መሪነት ጉዳዩን የተመለከተው ኮሚቴው ከእለቱ ዳኛ ሪፖርት በቀር፡ የኢኳቶሪያል ጊኒያዊዉን ኮሚሽነር ጉስታቮ ኤዱን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት ያቀረቧቸው ሪፖርቶች እና ምስክርነቶች የፋውዚ ሌክያን ጥፋተኛነት ለማረጋገጥ በቂ ሆነው አላገኘሗቸውም” ሲል በነጻ አሰናብቷቸዋል፡፡