የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ2020 የቻን አፍሪካ ዋንጫ የቅድመ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ከ ጂቡቲ አቻው ጋር የፊታችን ሀምሌ 19 ጅቡቲ ላይ ያከናውናል፡፡ ለዚህ ይረዳው ዘንድም ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ አዳማ ላይ ዝግጅቱን እያከናወነ ይገኛል፡፡

ይህንን በማስመልከትም የብሄራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ እና አምበሉ አስቻለው ታመነ በዛሬው እለት ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥተዋል፡፡

ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የተጨዋቾች ምርጫ እና ዝግጅታቸዉን በተመለከተ ‹‹23 ተጫዋቾች መርጠናል፡ በየቦታው ሁለትሁለት ተጨዋቾችን እና ሶስት ግብ ጠባቂዎች ነዉ የጠራነው፡ ልምምዳችንንም በቀን ሁለት ጊዜ አልፎ አልፎ ደግሞ አንድ ጊዜ አድርገን እየሰራን እንገናለን፡፡ ከአቡበከር ናስር እና አህመድ ረሽድ በቀር ሁሉም በመልካም ጤንነት ላይ ሲገኙ ሙጂብ ቃሲም ደግሞ በፓስፖርት ምክንያት አብሮን የማይጓዝ ይሆናል›› ሲሉ አስታውቀዋል፡ ፡

አሰልጣኙ አክለውም ይህንን ውድድር ለቻን ለማለፍ እና ለ2021 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎች ጠንካራ ቡድን ለመገንባት እንደሚጠቀሙበት ያስረዱ ሲሆን እግረ መንገዳቸውን ስለ 2021ዱ የአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድል ያላቸው ሀሳብ ምን እንደሆነ ተጠይቀው ሲመልሱ ‹‹ከኮትዲቯር ፡ ኒጀር እና ማዳጋስካር ጋር ነው የተደለደልነው፡ በመሆኑም ጠንካራ ምድብ ውስጥ እንዳለን እናምናለን፡ ምድቡን የሚመጥን ዝግጅት ማድረግ ከቻልን ግን ማለፍ እንደምንችል እርግጠኛ ነኝ፡፡ እንዲያውም ጠንካራ ምድብ ውስጥ መገኘታችን ለጠንካራ ዝግጅት ያነሳሳናል›› ብለዋል፡፡

የቡድኑ አምበል አስቻለው ታመነ በበኩሉ ‹‹በሊጉ መቆራረጥ ምክንያት መጠነኛ የአካል ብቃት ዝግጁነት ጉድለት ቢያጋጥመንም ለውድድሩ እና ተጋጣሚያችን ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ጥሩ ዝግጅት እያደረግን እንገኛለን፡፡ ማጣሪያውን አልፈን በውድድሩ ላይ ጥሩ ውጤት ካስመዘገብን በእግር ኳሱ ላይ ያለውን አመለካከት ለመቀየር እንደምንችል እምነት ስላለን በሚገባ እተዘጋጀን ነው፡፡ ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል፡፡

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *