ግንቦት 30/2011 ዓ.ም ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ  ዛሬ በፈረንሳይ፡ ፓሪስ እየተካሄደ በሚገኘው የአለም የሴቶች እግር ኳስ ጉባኤ ላይ በክብር እንግድነት በመገኘት ባደረጉት ንግግር፡ የስፖርት ሚዲያው ለሴቶች እግር ኳስ የሚሰጠውን ትኩረት እንዲያሻሽል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ፕሬዝዳንቷ ዛሬ ምሽት በፓሪስ ከሚጀመረው የ2019ኙ የፊፋ የሴቶች የአለም ዋንጫ አስቀድሞ በተዘጋጀው በዚህ መድረክ ላይ ለሴት እግር ኳስ ተጫዋቾችም “በምትሰሩት ሁሉ በጣም ልቃችሁ ተገኙ! ማንም አላየንም ማለት እንዳይችል አድርጉ! የዚህ አመት የፊፋ መሪ ቃል እንደሚለው ደምቃችሁ ታዩ!  ከሁሉ በላይ ሆናችሁ ተገኙ!” ሲሉ የማበረታቻ ምክራቸውን ለግሰዋቸዋል፡፡

የወቅቱ ብቸኛዋ አፍሪካዊት ርዕሰ ብሔር የሆኑት ክብርት ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በጉባኤው ላይ ያሰሙት ንግግር ከፊፋ ዋና ፀሀፊ ፋትማ ሳሙራ ጨምሮ በብዙዎች ዘንድ አድናቆት የተቸረው ነበር፡፡

በዚህ ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ እግር ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የሴቶች እግር ኳስ ብሔራዊ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ሶፊያ አልማሙን እና ኢትዮጵያዊቷ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የሴቶች እግር ኳስ ልማት ሀላፊ ወ/ሪት መስከረም ታደሰ ተገኝተዋል፡፡

በተጨማሪም ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት፡ ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ሊዲያ ታፈሰ በበኩሏ ውድድሩን እንዲመሩ በፊፋ ከተመረጡ ሶስት አፍሪካውያን ዳኞች መካከል አንዷ በመሆን ቀደም ብላ ፓሪስ መድረሷ ይታወሳል፡፡

 

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *