ሊጠናቀቅ የሶስት ሳምንታት እድሜ ብቻ የቀሩት የ2011ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ፡ በክለቦች፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የክልል ስፖርት ኮሚሽኖች እና ፌዴሬሽኖች አለመግባባት ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ ተቋርጧል፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንም በጉዳዩ ዙሪያ ተከታዩን መግለጫ አውጥቷል፡፡
የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በዛሬው ዕለት ባደረጉት አስቸኳይ ስብሰባ በ27ኛው ሳምንት መካሄድ የነበረበት የኢትዮጵያ ቡና እና የመቐሌ 70 እንደርታ ጨዋታ በፀጥታ ስጋት ምክንያት አለመካሄዱ በሊጉ ላይ የሚደርሰውን ተፅኖ በጥልቀት በመወያየት እና በመመርመር የሚከተሉትን ውሳኔዎች አስተላልፏል፡፡
1ኛ. ቀደም ሲል የሊግ ኮሚቴ በ27ኛ ሳምንት በኢትዮጵያ ቡና እና በመቐለ 70 እንደርታ መካከል ያለው ጨዋታ እንዲካሄድ የወሰነው ውሳኔ እንዲሻር እና በ29/09/11 ዓ.ም የሚካሄደው ጨዋታ እንዲቀር ፣
2ኛ. የቀጣዩ የኘሪሚየር ሊግ ውድድሮች በተገቢው መንገድ እንዲካሄድ ከክለቦች እና ከተለያዩ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተነጋግረን እና ተወያይትን ዘላቂ መፍትሄ እስኪሰጥ ድረስ ላልተወሰነ ጊዜ የወንዶች ፕሪሚየር ሊግ እንዲቋረጥ
3ኛ. የተለያዩ ወጪዎች እና ሌሎች ጉዳዮች በደንቡ መሠረት የሚጠየቁ ጥያቄዎች በፌዴሬሽኑ የዲስኘሊን መመሪያ የውድደር ደንብ መሠረት እንዲታዩ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡