የልዩ ስፖርት ድረ-ገጽ የፖድካስት መሰናዶውን የመጀመሪያ ክፍል ከአለማችን ‘የምንጊዜም ምርጥ የረጅም ርቀት ሯጭ’ እና የተሳካለት የንግድ ሰው አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ጋር አዝናኝ እና አስተማሪ ቆይታ በማድረግ ጀምሯል፡፡

ኃይሌ በዚህ መሰናዶ ከስኬታማ አትሌትነት ወደ ስኬታማ ነጋዴነት የነበረውን ሽግግር እና ፈተና፤  ስለ ኢትዮጵያውያን የስራ ባህል፤ ለዘመኑ ወጣት አትሌቶች ከራሱ ልምድ በመነሳት ከሩጫ በኋላ ስለሚጠብቃቸው ህይዎት እና ማድረግ ስላሉባቸው ጥንቃቄዎች ምክሩን ለግሷል፡፡

ኃይሌ ለወጣቶቹ አትሌቶች፡ “በጊዜ እወቁበት ምክንያቱም ገንዘቡ ለመጥፋት ሲሆን ከእናንተም ይፈጥናልና ይላል፡፡”

በተጨማሪም ስለ ቢዝነስ አርዓያው፡ ከ3000 በላይ ሰራተኞችን ቀጥሮ ስለሚያሰራው፡ በየአመቱ ለመንግስት በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ብሮችን  በግብር መልክ ስለሚያስገባው እና ከቢሊዮን ብሮች በላይ መዋዕለ ንዋይ ስለሚንቀሳቀስበት ቢዝነሱ፡ ከልቡ ስለሚወዳት ኢትዮጵያ እና በቀጣይ አዲስ ስለሚጀምራቸው የኢንቨስትመንት አይነቶች ብዙ የሚለን ይኖረዋል፡፡

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *