በኮትዲቯር አስተናጋጅነት ከሚያዝያ 8-12/2011 ዓ.ም
በተካሄደው የአፍሪካ ከ – 18 እና ከ – 20 አመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና በሁለቱም የእድሜ እርከኖች 111 ልኡካንን በመላክ (82 አትሌቶችን) የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን በአጠቃላይ ሜዳሊያ ብዛት 4ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቋል፡፡

ኢትዮጵያ በዚህኛው ውድድር ከዚህ ቀደም በውጤታማነት በማትታወቅባቸው እንደ የርዝመት ዝላይ እና መዶሻ ውርወራ አይነት የሜዳ ተግባር ውድድሮች ላይ ውጤታማ መሆን ብትችልም፡ ከዚህ ቀደም ውጤታማ በነበረችባቸው ውድድሮች ላይ ግን በኬንያ የበላይነት ተወስዶባታል፡፡

በሁለቱም የእድሜ ክፍሎች ውጤታማ የሆኑ ሀገራትን እና ያሸነፉትን የሜዳሊያ ብዛት ለማስታወስ ያክል፡

ከ 18 አመት በታች

1ኛ. ደቡብ አፍሪካ = 32
2ኛ. ኬንያ = 17
3ኛ. ናይጀሪያ = 16
4ኛ. ኢትዮጵያ = 11 (3 ወርቅ፡ 4 ብር: 4 ነሀስ)

ከ 20 አመት በታች

1ኛ. ኬንያ = 28
2ኛ. ደቡብ አፍሪካ = 25
3ኛ. ናይጀሪያ = 16 (7 ወርቅ)
4ኛ. ኢትዮጵያ = 22 (6ወርቅ፡ 4 ብር፡ 12 ነሀስ)

የልኡካን ቡድኑም ነገ ሰኞ ሚያዚያ 14/2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በኢትዮጵያ ሆቴል አቀባበል ይደረግለታል፡፡

ከአቢጃኑ ውድድር አንድ ቀን አስቀድሞ በተካሄደው የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን የምርጫ ጉባኤ ካሜሮናዊው ሀማድ ካልካባ ለአምስተኛ ጊዜ የኮንፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ሆነው በመመረጣቸው፡ ለቀጣዮቹ አራት አመታት የአፍሪካን አትሌቲክስ በበላይነት እንዲመሩ መሰየማቸውም ታውቋል፡፡

author image

About Liyusport.com

ልዩ ስፖርት ድረ-ገጽ የኢትዮጵያን ስፖርት እና ከባቢውን በመሰረታዊነት ሊለውጡ የሚችሉ የባለሙያ ሃሳቦች: ትችቶች፡ የምርምር ውጤቶች እና ሀተታዊ ጽሁፎች በራሳቸው በባለሞያወቹ ብዕር እና አንደበት ተዘጋጅተው በጽሁፍ እና በድምጽ የሚስተናገዱበት፡ እንዲሁም የምርመራ ጋዜጠኝነትን ጨምሮ ልዩ ልዩ የጋዜጠኝነት ውጤት የሆኑ ፅሁፎች የሚቀርቡበት እና በአይነቱ ልዩ የሆነ የስፖርት ድረ-ገፅ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You Might Also Like...