አዲስ አበባ – ሀምሌ 27/2014ዓ.ም ኢትዮጵያ  የምታስተናግደው የምስራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ (ሴካፋ) ከ17 አመት በታች ሻምፒዮና በቀጣዩ ዓመት መጀመሪያ አዲስ አበባ ላይ ይካሄዳል።  ውድድሩ ለክፍለ አህጉሩ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያነትም ያገለግላል።

የሴካፋ ዋና ዳይሬክተር አዉካ ጌቾ፡ ውድድሩ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በተደረሰው ስምምነት መሰረት፡ ከመስከረም 20 እስከ ጥቅምት 05/2015ዓ.ም በዋና ከተማዋ እንደሚካሄድ አረጋግጠዋል።

የውድድሩ የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት መስከረም 06/2015 ዓ.ም የሚከናወን ሲሆን፡ ተሳታፊ ሀገራት ደግሞ  እስከ ከመስከረም 16  ድረስ ወደ ኢትዮጵያ በመግባት በካፍ ቁጥጥር የማደረገውን የMRI ምርመራ ማካሄድ ይጠበቅባቸዋል።

ኢትዮጵያ በምታስተናግደው ይህ ተጠባቂ ውድድር አሸናፊ የሚሆነው ሀገር ምስራቅ አፍሪካን በመወከል አልጄርያ ለምታስተናግደው ከ17 ዓመት የአፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎን የሚያረጋግጥ ይሆናል ።

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *