በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አኩሪ ድል ላስመዘገቡት አትሌቶች እስከ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚደርስ ሸልማት ተበረከተ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 21፣ 2014 – በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አኩሪ ድል ላስመዘገቡ አትሌቶች ከ50 ሺህ ብር እስከ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚደርስ ሸልማት ተበረከተ፡፡

በአሜሪካ ኦሪገን በተካሄደው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተመዘገበውን አኩሪ ድል በማስመልከት የአትሌቶች የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል መርሐ-ግብር በብሔራዊ ቤተ-መንግስት እየተካሄደ ነው፡፡

በመርሐ – ግብሩ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በመድረኩ በ18 ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አኩሪ ድል ላስመዘገቡ አትሌቶች እና ሌሎች የልዑካን ቡድን አባላት ከ50 ሺህ ብር እስከ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር የሚደርስ ሽልማት ተበርክቷል፡፡

በሻምፒዮናው ለተሰንበት ግደይ በ10 ሺህ ሜትር የመጀመሪያውን ወርቅ በማስገኘቷ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር እና በ5 ሺህ ሜርት ላሳየችው ውጤታማ የቡድን ሥራ 500 ሺህ ብር በድምሩ የ2 ሚሊየን ብር ተሸላሚ ሆናለች፡፡

በተጨማሪም በሴቶች እና ወንዶች ማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ ላሸነፉት እና የውድድሩን ክብረወሰን ላሻሻሉት አትሌት ጎተይቶም ገብረስላሴ እና ታምራት ቶላ ለእያንዳንዳቸው የ1 ሚሊየን 750 ሺህ ብር ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

በ1 ሺህ 500 ሜትር የብር ሜዳሊያ እና በ5 ሺህ ሜትር የወርቅ ሜዳሊያ ያስገኘቸው ጉዳፍ ጸጋይ የእለቱ ከፍተኛ ሽልማት የሆነ የ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ተሸላሚ ሆናለች፡፡

በወንዶች ማራቶን ሁለተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ የብር ሜዳሊያ ያስገኘው ሞስነት ገረመው፣ በ3 ሺህሜ መሰናክል የብር ሜዳሊያ ያስገኘቸው ወርቅውሃ ጌታቸው እና በ3 ሺህ ሜ መሰናክል የብር ሜዳሊያ ላስገኘው ለሜቻ ግርማ እያንዳንዳቸው የ1 ሚሊየን ብር ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

በሻምፒዮናው የነሐስ ሜዳሊያ ላመጡ አትሌቶችም የ700 ሺህ ብር ሽልማት ተደርጎላቸዋል፡፡

ሽልማቱን የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ አበርክተዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም፡ በአለም ሻምፒዮናው ተሳትፈው ሜዳሊያ ላመጡ አትሌቶች የመሬት ሽልማት አበረክቷል።

በዚህም መሰረት:

– አትሌት ለተሰንበት ግደይ 500 ካሬ

– አትሌት ጎተይቶም ገ/ስላሰ 500 ካሬ

– አትሌት ታምራት ቶላ 500 ካሬ

– አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ 500 ካሬ

– አትሌት ወርቅውሃ ጌታቸው 350 ካሬ

– አትሌት ለሜቻ ግርማ 350 ካሬ

– አትሌት ሞስነት ገረመው 350 ካሬ

– አትሌት ዳዊት ስዩም 250 ካሬ

– አትሌት መቅደስ አበበ 250 ካሬ

ለመላው የልዑካን ቡድኑ አባላት ደግሞ የአስር ሚሊዬን ብር የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል::

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *