ሀዋሳ ጥር 06/2014 ዓ.ም – የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 25ኛ አመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በሀዋሳ ገዛኸኝ እና እልፍነሽ ሆቴል ማካሄድ ጀምሯል።

ከጉባኤው መጀመር አስቀድሞ በህልውና ዘመቻው ለተሰው ወገኖች የአንድ ደቂቃ የህሊና ጸሎት የተደረገ ሲሆን፣ በዘመቻው ለተሳተፉ የአትሌቲክሱ ቤተሰቦች፡ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ፣ ፈይሳ ሌሊሳ፣ ገዛኸኝ አበራ፣ ማርቆስ ገነቴ እና ፋንቱ ሜጌሶ በጠቅላላ ጉባኤው ስም እውቅና ተሰጥቷል።

ጉባኤውን በንግግር ያስጀመሩት የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ኮ/ር ደራርቱ ቱሉ በበጀት አመቱ የተከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን እና ያጋጠሙ ፈተናወችን ለጉባኤው አቅርበዋል።

በጉባኤው መክፈቻም የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ቀጀላ መርዳሳ፣ ሚንስትር ዲኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና የቀድሞው የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ብስራት ጋሻው ጠናን ጨምሮ ልዩ ልዩ እንግዶች ተገኝተዋል።

ለሁለት ቀናት በሚካሄደው ጠቅላላ ጉባኤ የመጀመሪያ ቀን ውሎ፡ የ2013 ዓ.ም የበጀት አመት የዕቅድ እና ፋይናንስ አፈጻጻም ሪፖርት፣ የኦዲት ሪፖርት ማድመጥ፡ በበጀት አመቱ የተከናወኑ አበይት የአትሌቲክስ ክንውኖች ላይ ውይይት ማድረግ፣ በፌዴሬሽኑ ባለቤትነት የተዘጋጁ የኢትዮጵያን አትሌቲክስ እና ውድድሮቹን የሚዘክሩ መጻሕፍት ምርቃት እና የ2014 ዓ.ም ዕቅድና በጀት ላይ መወያዬት በአጀንዳነት ከተያዙ ዋናዋና ጉዳዮች መካከል ናቸው።

በጉባኤው የሁለተኛ ቀን ውሎ ደግሞ የአትሌቲክስ አሰልጣኞች ስታንዳርድ፣ የብሔራዊ ቡድን አትሌቶች እና አሰልጣኞች መምረጫ መስፈርት፣ የባለድርሻ ተገልጋዮች ድጋፍ አሰጣጥ እና የሽልማት አሰጣጥን የሚወስኑ ልዩ ልዩ መመሪያወችን አቅርቦ መወያዬት መርሃግብር የተያዘላቸው አጀንዳዎች መሆናቸውን ከወጣው መርሃግብር መረዳት ይቻላል።

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *