መጋቢት 18/2013 ዓ.ም – በኢንተርኮንቲኔንታል አዲስ ሆቴል በተካሄደው የውድድር አመቱ የ16 ሳምንታት ጨዋታዎች ግምገማ እና ውይይት ላይ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትን ጨምሮ፡ ከ13ቱ የሊጉ ባለ አክሲዮን ክለቦች የ10ሩ አመራሮች (ስራ አስኪያጅ፣ ቡድን መሪ ወይም አሰልጣኝ ብቻ) ተገኝተዋል።

የዕለቱ የክብር እንግዳ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ የሊግ ኮሚቴው ውድድሩን የመራበት ሂደት አድናቆት የሚገባው ነው ሲሉ አድናቆታቸውን ገልጸዋል። ፕሬዝዳንቱ አክለውም፡ በሊጉ ዳኝነት ላይ መሻሻሎችን ለማምጣት ተጠሪነቱ ለፌዴሬሽኑ የሆነውን የዳኝነት ኮሚቴ አመራሮችን መቀየሩንም አስታውቀዋል።

የሊግ ኮሚቴው የቦርድ ፕሬዝዳንት ፻ አለቃ ፈቃደ ማሞ ፉክክሩ በቀጣይ የሚካሄድባቸው ሀዋሳ እና ድሬዳዋ በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ በኮቪድ ወረርሽኝ ምክንያት ቀዳሚዎቹ አካባቢዎች መሆናቸውን በማስታወስ፡ ውድድሩ በወረርሽኙ ምክንያት እንዳይቋረጥ ክለቦቻችን ትልቅ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

የሊጉ የእስካሁኑ ጉዞ በቁጥር ሲገለፅ

– 96 ጨዋታ
– 38 ዋና ዳኞች
– 38 ረዳት ዳኞች
– 24 ታዛቢዎች
– 241 ጎሎች ተቆጥረዋል
– 205ቱ በጨዋታ፣ 33ቱ ደግሞ በቅጣት ምት ሲሆኑ ሶስቱ ደግሞ በራስ ላይ የተቆጠሩ ናቸው

በውይይቱ ላይ ከክለቦቹ ከተነሱ ሀሳቦች መካከል፡

ሁሉም ተናጋሪዎች ከሀሳባቸው አስቀድሞ ሊግ ኮሚቴው ውድድሩን በብቃት ለመራበት መንገድ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

 • ውድድሩ በዚህ መንገድ (Format) ቢቀጥል
 • የውድድር ሜዳ መረጣ ጉዳይ ጥራትን ያማከለ ቢሆን
 • ወደ ሜዳ የሚገቡ ተመልካቾች ቁጥር ከተገቢው ጥንቃቄ ጋር ቢጨመር
 • በተደጋጋሚ ጨዋታዎች ብዛት ተጫዋቾች ለጉዳት እና ድካም እየተጋለጡ ስለሆነ የተጫዋቾች ቅያሬ ቁጥር ከሁን ካለበት ሶስት ወደ አራት/አምስት ከፍ ቢል
 • የመለማመጃ ሜዳዎች አቅርቦት እና የሰዓት ድልድል ጉዳይ ቢታሰብበት
 • ውድድሩ በቴክኒክ ባለሞያዎች ቢገመገም
 • የድሬደዋ ጨዋታዎች ከሙቀቱ አንጻር እና ካለው የተሟላ የስቴዲየም መብራት በመነሳት ሁሉም ጨዋታዎች ምሽት ቢደረጉ
 • የዝውውር መስኮቱ ውድድሩ ከቆመ በኋላ አጋማሽ ላይ ቢከፈት
 • የዳኝነት ችግሮች አሉ ነገር ግን ለእነሱስ ምን እገዛ ተደርጓል?
 • የውድድር አመቱ ኮከቦች ሽልማት ጉዳይ ላይ ምን እየተሰራ ነው

ከአወዳዳሪ አካላት ከተሰጡ ምላሾች መካከል፡

 • አመቱ መጫረሻ ላይ ከብሮድካስተሩ ጋር ባለን ስምምነት መሰረት የአሰልጣኞች እና የዳኞች ስልጠናዎች ይኖሩናል።
 • የወራጃ ክለቦችን ጉዳይ፡ በተመለከተ በመተዳደሪያ ደምባችን መሰረት የሚወጡ እና የሚወርዱ ክለቦች ይስተናገዳሉ።
 • የዳኝነት ጥራትን በተመለከተ ለማሻሻል እየሰራን ነው።
 • የድሬዳዋዉ ጨዋታ ሁሉም ከሰዓት በኋላ ቢሆን ለሚለው፡ ከቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት እና ሌሎች ሁኔታዎች ጋር በተያያዘ ስላልተመቸን አሁን ባለው መንገድ የጠዋቱ ጨዋታ 3:00 ላይ የከሰዓቱ ጨዋታ ደግሞ 11:00 ላይ ይከናወናል።
 • የኮከቦች ሽልማትን በተመለከተ አለምአቀፍ አሰራርን ተከትሎ ይከናወናል።
author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *