አዲስ አበባ – መስከረም 18/2013ዓ.ም – በአትሌቲክስ ስፖርት አፍቃሪዎች ዘንድ በከፍተኛ ጉጉት እየተጠበቀ በሚገኘው የ2020 ለንደን ማራቶን ላይ የሚሳተፉ የኢትዮጵያ እና ኬንያ አትሌቶችን የያዘው፡ ባለ 56 ቢዝነስ ክላስ መቀመጫው የኦሪክስ 737-500 ቦይንግ ቻርተርድ አውሮፕላን ትላንት ምሽት ከአዲስ አበባ ተነስቶ ለንደን ገብቷል፡፡

በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት አዋቂ አትሌቶች ብቻ የሚሳተፉበት እና ታላላቆቹ ቀነኒሳ በቀለ፣ ኤሉድ ኪፕቾጌ፣ ሞስነት ገረመው፣ ሙሌ ዋሲሁን፣ ታምራት ቶላ እና ሹራ ኪታታ በወንዶቹ፣ ሩት ቼፔንጌቲቺ፣ ብሪጂድ ኮስጌይ፣ ቪቪያን ቼሪዮት፣ አሸቴ በከሪ እና መገርቱ አለሙን የመሳሰሉ አትሌቶች በሴቶች ምድብ የሚካፈሉበት ውድድር የፊታችን እሁድ መስከረም 24/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ይካሄዳል፡፡

በኢትዮጵያ በኩል በዚህ ውድድር ላይ ለማካፈል በአጠቃላይ 11 አባላት ያሉት የልኡክ ቡድን ወደስፍራው ተጉዟል፡፡ ከእነዚህም መካከል ሶስቱ አሰልጣኞች ሲሆኑ የተቀሩት ደግሞ አትሌቶች ናቸው፡፡

ልዩ ስፖርት ባገኘችው የተረጋገጠ መረጃ መሰረት በዚህ ውድድር ላይ መካፈል የነበረባቸው የተወሰኑ አትሌቶች እና አሰልጣኝ በግል ጉዳይ ምክንያት ወደ ስፍራው ያልተጓዙ ሲሆን ወደ ለንደን ከተጓዙት አትሌቶች መካከልም፡ በፊትነስ እና ሌሎችም ምክንያቶች ውድድሩ ላይ ስለመሳተፋቸው የመጨረሻ ውሳኔያቸውን እንዲያሳውቁ የሚጠበቁ አትሌቶች እንዳሉም ለማወቅ ችለናል፡፡

ቀነኒሳ በቀለ ከ ኤሊዩድ ኪፕቾጌ

የአለም የማራቶን ክብረወሰን ባለቤቱ (02:01:39) ኬንያዊዉ ኤሊዩድ ኪፕቾጌ እና በሁለት ሰከንዶች ብቻ አንሶ ሁለተኛው የርቀቱ የምርጥ ሰዓት ባለቤቱ ቀነኒሳ በቀለ እርስ በእርስ ሲገናኙ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜያቸው አይደለም።

ይልቁንም እኤአ ከ2003ቱ የኦስሎ የ5000ሜ የጎልደን ሊግ ውደድር ጀምሮ በትራክ በሀገር አቋራጭ እና በማራቶን ውድድሮች ለ24 ጊዜያት ያክል አብረው ሮጠዋል።

ከዚህ በመቀጠል ባለፉት 17 አመታት እርስ በእርስ ባደረጓቸው ውድድሮች ያስመዘገቧቸውን ውጤቶች ምን እንደሚመስሉ ለማሳዬት እወዳለሁ።

– በአጠቃላይ በትራክ፣ ሀገር አቋራጭ እና የማራቶን ውድድሮች ለ24ጊዜያት ያክል አብረው ሮጠዋል።

– ከ24ቱ ውድድሮች በ18ቱ ሁለቱ አትሌቶች ሲያሸንፉ የተቀሩትን ደግሞ በሌሎች ተቀድመው ውድድሩን ጨርሰዋል።

– ቀነኒሳ በቀለ 13 ጊዜ ውድድሮቹን በአንደኛነት አጠናቋል

– ኤሊዩድ ኪፕቾጌ በበኩሉ ለአምስት ጊዜያት ያክል አሸንፏል።

– ከ24ቱ ውድድሮች ቀነኒሳ 15 ጊዜ ፣ ኪፕቾጌ ደግሞ 9ጊዜ አንዳቸው ከአንዳቸው ቀድመው ገብተዋል።

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *