አዲስ አበባ – ነሀሴ 25/2012 ዓ.ም – ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ 45 የአፍሪካ ሀገራት ላለፈው ሩብ ክፍለ ዘመን ያክል በአህጉሪቱ የዲጂታል አለም መዝናኛ ዘርፍ ተሰማርቶ የቆየው መልቲቾይዝ ኩባንያ፡ አሁን ደግሞ የኢትዮጵያውያን ተመልካቾቹን የመዝናኛ ፍላጎት ሊያረኩ ይችላሉ ያላቸውን አዳዲስ የፕሮግራም ማዕቀፎችን ከተሻሻሉ የክፍያ መጠኖች ጋር ይዞ መምጣቱን አስታውቋል።

መልቲ ቾይዝ ኢትዮጵያ “እኛን የሆነው ማነው?” በሚል ዘመቻ ሲያስተዋውቅ የቆየውን እና በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውን አዲሱን የዲ ኤስ ቲቪ ፓኬጅ፡ ዛሬ ረፋድ ላይ በህያት ሪጀንሲ ሆቴል ባከናወነው ፕሮግራም ይፋ አድርጓል።

በመርሃ ግብሩ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የመልቲ ቾይዝ ኢትዮጵያ ማኔጅንግ ዳይሬክተር ገሊላ ገብረሚካኤል “ላለፉት አመታት ተመልካቾቻንን ምን ያስደስታቸዋል? በማለት ባደረገነው ጥናት ተመስርተን፡ ዲ ኤስ ቲቪን የበለጠ ኢትዮጵያዊ ለማድረግ ጥረት አድርገናል። በዚህም መሰረት ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ተደራሽ የሚያደርጉ ኮንተንቶችን ተመጣጣኝ በሆነ ክፍያ የሚያቀርቡ ልዩ ልዩ ፓኬጆችን አቅርበናል” ብለዋል።

ዲ ኤስ ቲቪ ሜዳ (በወር 550ብር)፣ ጎጆ (ብር 220) እና ቤተሰብ (ብር 380) የተሰኙ አዳዲስ ፓኬጆችን ይዞ የመጣ ሲሆን፤ በስራቸውም በአማርኛ ብቻ የሚተላለፉ እንደ ትሬስ ሚዩዚክ፡ የኢትዮጵያ ሙዚቃዎች ቻናል፣ ኒኮሎዲያን፡ የህጻናት ቻናል፣ ዚ ዓለም፡ (የውጪ ሀገር የትርጉም ፊልሞች የሚታዩበት ቻናሎች) እንደሚኖሩበት ለማወቅ ተችሏል።

በተጨማሪም 14 የሀገር ውስጥ የቴሌቪዥን ቻናሎች፣ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1፣ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 እና አሀዱ ኤፍ ኤም 94.3፣ እንዲሁም በቅርቡ የሚጀምረውን ሱፐር ስፖርት አማርኛን ጨምሮ ልዩ ልዩ ኦሪጂናል ኢትዮጵያዊ የመዝናኛ ኮንተንቶችን የሚያካትት መሆኑ ተገልጿል።

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *