የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ለአባል ሀገራቱ ባሰራጨው መረጃ መሠረት በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ወደ 2022 ለተጨማሪ ስድስት ወራት የተራዘመው የካሜሮኑ የአፍሪካ ዋንጫ ቀሪ የምድብ ጨዋታዎች ከቀጣዩ አመት ህዳር ወር ጀምሮ እንደሚከናወኑ አስታውቋል።

በዚህም መሰረት ከመስከረም 25 – ጥቅምት 3/ 2013 ዓ.ም ያሉትን ቀናት ብሔራዊ ቡድኖች ተጫዋቾቻቸውን ማግኘት የሚቻሉባቸው ቀናቶች መሆናቸውን የገለፀ ሲሆን፡

ከጥቅምት 30 – ህዳር 8/2013 ዓ.ም – የየምድቦቹ ሶስተኛ እና አራተኛ ጨዋታዎች (ኢትዮጵያ ከ ኒጀር – ደርሶ መልስ)

ከመጋቢት 13 -21/2013 ዓ.ም ደግሞ የአምስተኛ እና ስድስተኛ የየምድቦቹ ጨዋታዎች የሚከናወኑ ይሆናል። ( ኢትዮጵያ ከማዳጋስካር እና አይቮሪኮስት ከ ኢትዮጵያ)

ለሶስት ጊዜያት ያክል የውድድሩ ቀን በተቀያዬረውና በጥር 2014 ዓ.ም እንደሚከናወን ቀጠሮ በተያዘለት 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ፡ አይቮሪኮስትን ባህር ዳር ላይ 2ለ1 ያሸነፈችው ኢትዮጵያ፡ ምድቡን በስድስት ነጥብ ከምትመራው ማዳጋስካር በሶስት ነጥብ ዝቅ ብላ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

ካፍ ለአባል ሀገራቱ በላከው መረጃ ጨምሮ እንዳስታወቀው፡ የአፍሪካ ክፍለ አህጉር የ2022 ኳታር የዓለም ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታወችም ከግንቦት 2013 እስከ ህዳር 2014 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት እንደሚከናወኑ ይፋ አድርጓል።

በቅድመ ማጣሪያው ሌሴቶን ከሜዳ ውጭ ባገባ በሚለው ህግ (1ለ1) በመጣል ያለፈችው ኢትዮጵያ፡ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫ ተሳትፎን ለማግኘት በምድብ ሰባት ከ ጋና፣ ደቡብ አፍሪካ እና ዚምባቡዌ ጋር መደልደሏ ይታወቃል።

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *