የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ረፋድ ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ባደረገው አስቸኳይ የቴሌ ኮንፈረንስ፡ ሁሉንም የ2012 ዓ.ም የእግር ኳስ ውድድሮች ለመሰረዝ ውሳኔ ማሳለፉን አሳውቋል።

ፌዴሬሽኑ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር መገኘቷ እና ወረርሽኙ መቼ እንደሚጠፋ ባለመታወቁ: ከመንግስት እና ከፕሪሚየር ሊጉ አብይ ኮሚቴ ጋር ባደረገው ውይይት መሰረት የሚከተተሉትን ውሳኔዎች ማሳለፉን ይፋ አድርጓል።

ውሳኔዎቹም:

1. የ2012 ዓ.ም ሁሉም የሊግ ውድድሮች ሙሉበሙሉ ተሰርዘዋል።

2. በየትኛውም ሊግ ውስጥ አሸናፊ አይኖርም

3. በየትኛውም የሊግ እርከን ውስጥ ማደግ እና መውረድ አይኖርም

4. በቀጣይ አመት በከፍ ቻምፒዮንስ ሊግ እና ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ውድድሮች ኢትዮጵያን የሚወክሉ ክለቦች አይኖሩም

5. እስከ አመቱ መጨረሻ ያሉ ኮንትራቶች እንዲከበሩ

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *