የአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን በዚህ አመት የካቲትት ወር መጨረሻ ላይ ማከናወን ለሚጀምረው የአፍሪካ አትሌቲክስ ቱር፣ ውድድሩን እንዲያዘጋጁ ከመረጣቸው ስድስት ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን አሳውቋል።

ይህንን አይነት ውድድር ለማዘጋጀት ከተፈለገበት ዋና ዋና ምክንያቶች መካከልም፡ አፍሪካውያን አትሌቶችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያገለለ የመጣውን የዲያሞንድ ሊግ ውድድር ጫናን ለመቋቋም እና በአለም አቀፍ ደረጃ ብዙም ትኩረት የማይሰጣቸውን ነገር አፍሪካውያን አትሌቶች ውጤታማ የሆኑባቸውን የርቀት አይነቶችን ከፍ ባለ የጥራት እና የፉክክር ደረጃ ለማዘጋጀት እንደሆነ ተገለጿል።

ከየካቲት 24 እስከ ግንቦት 24/2012 ዓ.ም በእያንዳንዱ አዘጋጅ ሀገር ለአንድአንድ ቀናት የሚከናወነውን ይህንን የቱር ውድድር፡ ኮንጎ ብራዛቪል፣ ጂቡቲ፣ ኬንያ፣ ደቡብ አፍሪካ እና ካሜሩን፡ ከኢትዮጵያ በተጫማሪ እንደሚያዘጋጁት ኮንፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

የወድድሮቹ ትክክለኛ ቀናት እና የየዕለቱ የውድድር አይነቶችም በቀጣዮቹ ጊዜያት ይፋ እንደሚሆኑ ይጠበቃል።

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *