አዲስ አበባ – ጥቅምት 25/2012ዓ.ም – የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ “ኦሊምፒክ ኮሚቴው የሚጓዝበት መስመር እና ውሳኔዎች የሚተላለፉባቸው መንገዶች ግልጽ የሆነ አሰራርን የማይከተሉ: መመሪያ እና አሰራርን ሳይሆን የግለሰቦች ፍላጎትን ብቻ መሠረት አድርገው የሚካሄዱ እንዲሁም በአጠቃላይ ስፖርቱ እውነተኛ ተቆርቋሪ አጥቷል” ሲሉ የቅሬታቸውን መንስኤ ይገልጻሉ።

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ በበኩላቸው “የነገው ስብሰባ ደምቦች ላይ ለመመካከር የተጠራ ሲሆን፡ ምንም የተፈጸመ ስህተት የለም” ሲሉ ዛሬ ረፋድ ላይ በተላለፈው ዕለታዊዉ የ”ሸገር ስፖርት” የሬዲዮ ፕሮግራም ላይ ገልጸዋል።

ይሁንና ነገ ጠዋት በአምባሳደር ሆቴል እንደሚካሄድ ቀጠሮ የተያዘለት አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ/ ስብሰባ ላይ ተሰብሳቢዎቹ የተጠሩበት ሂደት እና የጉባኤው አጀንዳዎች በግልጽ ምንምን እንደሆኑ ቀደም ብለው አለመታወቃቸው፡ ከኮሚቴው መተዳደሪያ ደምብ እና አሰራር ጋር አብሮ የሚሄድ እንዳልሆነ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያ ይገልጻሉ።

ቀጥሎ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጊዚያዊ ፕሬዝዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ፡ በኦሊምፒክ ኮሚቴው ፕሬዝዳንት እና አሰራር ላይ ያቀረቡት ሶስት ገጽ የቅሬታ ደብዳቤ አያይዘናል።

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *