ዶሃ –  ኳታር – መስከረም 24/2012ዓ.ም – አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ 2፡10፡40 በሆነ ሰዓት የአለም ሻምፒዮናውን የወንዶች ማራቶን ውድድር አሸነፈ፡፡  ሌሊሳ ድሉን ተከትሎ በዶሃው ሻምፒዮና ለኢትዮጵያ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ ሲያሸንፍ፡  ከእርሱ በአራት ሰከንዶች ብቻ ዘግይቶ በመግባት ሁለተኛ የወጣው፡ የሀገሩ ልጅ ሞስነት ገረመው በበኩሉ የብር ሜዳሊያውን አሸንፏል፡፡ አትሌት ሙሌ ዋሲሆን ደግሞ ውድድሩን በጊዜ አቋርጦ ወጥቷል፡፡

ሌሊሳ ሊገባደድ አንድ ቀን ብቻ በቀረው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ያስመዘገበው የወርቅ ሜዳሊያ፡  ለኢትዮጵያ በውድድሩ ታሪክ የርቀቱ ሁለኛው እና ከ2001ዱ የገዛኸኝ አበራ የኤድመንተን ድል በኋላ የተገኘ ከፍተኛው ውጤት ነው፡፡

አትሌቱ ብርቱ ፉክክር የተደረገበትን እና ከሰሞኑ እጅግ የተሻለ የአየር ጸባይ የነበረውን ይህንን  ውድድር በማሸነፍ፡ ከስድስት አመታት በፊት በሞስኮው የአለም ሻምፒዮና በዩጋንዳዊው አትሌት ስቴፈን ኪፕሮቲች ለጥቂት  ተቀድሞ ያጣውን የወርቅ ሜዳሊያ ድል ያካካሰበትን ውጤት ለማስመዝገብ ችሏል፡፡

የኢትዮጵያውያኑን አትሌቶች የወርቅ እና ብር ሜዳሊያ አሸናፊነት ተከትሎ፡ በእረፍት ማጣት ስሜት ህመም ላይ የምትገኘው እና “የአትሌቶቹን መጨረሻ ሳላይ ወደ ማረፊያዬ አልሄድም” በማለት እስከ ሌሊቱ 9፡00 ድረስ በውድድሩ ስፍራ የቆየችው የፌዴሬሽኑ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉ፡ ደስታዋን በእምባ ስትገልጽ ታይታለች፡፡

አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ እና ሞስነት ገረመው ከውድድሩ በኋላ የሰጡትን አስተያት ቀጥሎ ካለው የቪዲዮ ሊንክ መመልከት ይቻላል፡፡

ዛሬ በተከናወኑ ሌሎች የፍጻሜ ውድድሮች በ1500ሜ የተሳተፈችው አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ ለሀገሯ የነሀስ ሜዳሊያ ስታሸንፍ፤ በ5000ሜ ፍጻሜ የተሳተፉት አትሌት ጸሀይ ገመቹ፡ ፋንቱ ወርቁ እና ሀዊ ፈይሳ በቅድም ተከተል ውድድራቸውን 4ኛ፣ 6ኛ እና 8ኛ በመሆን አጠናቀዋል፡፡

የመጨረሻው እለት የኢትዮጵያውያን አትሌቶች የውድደር መርሃግብር

10000ሜ ወንዶች

ተሳታፊ አትሌቶች – ሀጎስ ገብረህይዎት፣ ዮሚፍ ቀጀልቻ እና አንዳምላክ በልሁ

ሰዓት – ምሽት 2፡00

 

የኢትዮጵያ የዓለም ሻምፒዮናው የእስከዛሬ የማራቶን ውጤቶች

√ 2 የወርቅ ሜዳሊያ         – ገዛኸኝ አበራ – 2001 – ኤድመንተን

– ሌሊሳ ዴሲሳ – 2019 – ዶሃ

√ 5 የብር ሜዳልያዎች      – ከበደ ባልቻ – 1983 – ሄልስንኪ
– ሌሊሳ ደሸሲሳ – 2013 – ሞስኮ
– የማነ ጸጋዬ – 2015 – ቤይጂንግ
– ታምራት ቶላ – 2017 – ለንደን

–  ሞስነት ገረመው – 2019 – ዶሃ
√ 3 የነሀስ ሜዳሊያዎች    – ጸጋዬ ከበደ – 2009 – በርሊን
– ፈይሳ ሌሊሳ – 2011 – ዴጉ
– ታደሰ ቶላ – 2013 – ሞስኮ

 

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *