ዶሃ – ኳታር – መስከረም 21/2012ዓ.ም – ስድስተኛ ቀኑን በያዘው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና፤ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለት የማጣሪያ ውድድሮች ተሳትፈው በመልካም ውጤት ለማጠናቀቅ ችለዋል።
ከቀኑ 11:35 ሲል በ1500ሜ ሴቶች የማጣሪያ ተሳትፏቸውን ካደረጉት አትሌቶች መካከል ጉዳፍ ጸጋዬ እና ለምለም ሀይሉ ወደ ነገ ሌሊት 5:00ቱ የግማሽ ፍጻሜ ውድድር ሲያልፉ: አክሱማዊት እምባዬ ለጥቂት ከማጣሪያው ሳታልፍ ቀርታለች።
ጉዳፍ ከምድብ ሁለት 4:08.39 በሆነ ሰዓት ሶስተኛ ሆና ስታጠናቅቅ፡ ለምለም ሀይሉ በበኩሏ ከምድብ አንድ በ4:05.61 ሰባተኛ በመሆን ውድድሯን ጨርሳለች። በሶስተኛው ምድብ የተካፈለችው አክሱማዊት እምባዬ ደግሞ (4:08.56) ዘጠንኛ ሆና በማጠናቀቋ ነበር ወደ ፍጻሜው ሳታልፍ የቀረችው።
በ5000ሜ ሴቶች ማጣሪያ የተሳተፉት ሶስቱም ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ውድድራቸውን በስኬት በማጠናቀቅ ወደ ቅዳሜ ምሽት 3:25ቱ ፍጻሜ አልፈዋል።
አትሌት ጸሀይ ገመቹ የሁለተኛውን ምድብ ማጣሪያ 15:01.57 በሆነ ሰዓት በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ፣ በዚሁ ምድብ የተወዳደረችው ፋንቱ ወርቁ በ15:02.74 በስድስተኛነት፤ በመጀመሪያው ምድብ የተፎካከረችው ሀዊ ፈይሳ በበኩሏ በ14:53.85 ሶስተኛ በመውጣት ነው ፍጻሜውን መቀላቀላቸውን ያረጋገጡት።
እስከ ዛሬው ዕለት ድረስ ያለው የሜዳሊያ ሰንጠረዥ