ዶሃ – ኳታር – መስከረም 17/2012 ዓ.ም – አትሌት ለተሰንበት ግደይ በ10,000ሜ ርቀት የመጀመሪውን ሜዳሊያ ለሀገሯ አሸነፈች፡፡ እጅግ ጠንካራ ፉክክር በታየበት በዚህ ውድድር ለተሰንበት፡ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሆላንዳዊት ሲፋን ሀሰንን ተከትላ በመግባት ነው የብር ሜዳሊያ ባለቤት የሆነችው፡፡

በ10000 ሜትር ርቀት ሶስተኛ ተሳትፎዋን ያደረገችው አትሌቷ፡ ውድድሩ ሊጠናቀቅ አምስት ዙሮች ሲቀሩት ተፈትልካ በመውጣት እና ዙሩን በማክረር፡ የግል ምርጥ ሰዓቷን (30፡21.23) በማስመዝግብ በሁለተኝነት ለማጠናቀቅ ችላለች፡፡

40,000 ተመልካች በሚይዘው ካሊፋ ኢንተርናሽናል ስቴዲየም ጎልቶ በሚሰማ የኢትዮጵያውያን ደማቅ የድጋፍ ድባብ ታጅቦ በተከናወነው በዚህ ፉክክር፡ ሌላኛዋ የሀገሯ ልጅ ሰንበሬ ተፈሪ ውድድሩን በስድስተኛነት ስታጠናቅቅ፤ ነጻነት ጉደታ ደግሞ ውድድሩን አቋርጣ ወጥታለች፡፡

አትሌቷ ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ ‹‹ለሻምፒዮናው ጠንካራ ልምምድ ሳደርግ ቆይቻለሁ፤ እቅዴም ሜዳሊያ ውስጥ መግባት ነበር ተሳክቶልኛል፤ ለዚህ ውጤት ደግም የአሰልጣኘ ሐይሌ እያሱ ሚና በጣም ትልቅ ስለነበር ላመሰግነው እወዳለሁ‹‹ ስትል አስተያዬቷን ሰጥታለች፡፡

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *