የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በፕሪሚየር ሊግ ዙሪያ ከቀጣዩ የውድድር ዘመን (2012 ዓ.ም) ጀምሮ የፎርማት እና የተሳታፊ ክለቦች ቁጥር ላይ ለውጥ ሊኖር እንደሚችል አሳውቋል።

እንደ ፌዴሬሽኑ ሀሳብ ከሆነ ሊጉ በሁለት ምድብ እንዲከፈል እና በእያንዳንዱ ምድብ 12 ክለቦች፡ በድምሩ ደግሞ 24 ክለቦች የሚሳተፉበት ይሆናል።

በዚህም መሰረት በ2011ዓ.ም በሊጉ ተሳታፊ የነበሩ 16ቱም ክለቦች የሊጉ ክለብነታቸውን ይዘው የሚቆዩ ሲሆን በተጨማሪም ከከፍተኛ ሊጉ ያደጉት ሶስቱም ክለቦች፡ በከፍተኛ ሊጉ በየምድባቸው ሁለተኛ ሆነው ያጠናቀቁት ሌሎች ሶስቱ ቡድኖች እና ከየምድባቸው በተሻለ ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ያጠናቀቁ ሁለት ክለቦች ቀሪዎቹን ስምንት ቦታዎች እንደሚሞሉ ተገልጿል።

አዲሱ የሊግ ፎርማት እና የክለቦች ቁጥር ጉዳይ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ከመሆኑ በፊት ግን ፌዴሬሽኑ እና የሊጉ ተሳታፊ ክለቦች ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል።

© ልዩ ስፖርት፡ በዚህ ጉዳይ ዙሪያ በቀጣዮቹ ቀናት ተጨማሪ የባለሞያ ሀሳቦችን ይዛ ትመጣለች

author image

About Liyusport.com

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *