• ልዩ ስፖርት ድረ-ገጽ የኢትዮጵያን ስፖርት እና ከባቢውን በመሰረታዊነት ሊለውጡ የሚችሉ የባለሙያ ሃሳቦች: ትችቶች፡ የምርምር ውጤቶች እና ሀተታዊ ጽሁፎች በራሳቸው በባለሞያወቹ ብዕር እና አንደበት ተዘጋጅተው በጽሁፍ እና በድምጽ የሚስተናገዱበት፡ እንዲሁም የምርመራ ጋዜጠኝነትን ጨምሮ ልዩ ልዩ የጋዜጠኝነት ውጤት የሆኑ ፅሁፎች የሚቀርቡበት አዲስ እና በአይነቱ  ልዩ የሆነ የስፖርት ድረ-ገፅ ነው፡፡

እነማን ይጽፋሉ፡

 • ልዩ ልዩ ባለሞያዎች፣ ጋዜጠኞች፣ አሰልጣኞች፣ ስፖርተኞች፣ አስተዳዳሪዎች፣ አጥኚዎች፣ እና ደጋፊዎች ወዘተ…

እንዴት፡

 • ማንኛውም የኢትዮጵያን ስፖርት በሚመለከት ይጠቅማል የሚል  ሃሳብ ያለው ግለሰብ ጽሁፎቹን በማንኛውም ሰዐት ወደ ድረ-ገጹ በመላክ ማሳተም የሚችል ሲሆን፡ ነገር ግን ጽሁፎቹን ተከትለው ለሚቀርቡ በጎ ሀሳቦች ወይም ትችቶች፡ ሙሉ ሃላፊነቱን ራሱ/ሷ ጸሀፊው/ዋ የሚወሰድ/ትወስድ ይሆናል፡፡

ድረ-ገጹ አላማ – ክፍተቱን መሙላት!

 • በሀገራችን በርካታ ሁነት ተኮር የሆኑ እንደዚህ አሉ/ተባለ የሚሉ የስፖርት መሰናዶዎች በብዛት ይገኛሉ፡፡ ይህ ድረ-ገጽ ደግሞ በዋናነት እንዲህ ቢደረግ/ይደረግ የምንልበት ነጻ የሀሳብ ማንጸባረቂያ መድረክን ለማመቻቸት
 • ከስፖርቱ ጋር በአንዱም ይሁን በሌላኛው መንገድ ትስስር ያላቸው አካላት ለሁለንተናዊ የስፖርቱ እድገት ይበጃል የሚሉትን ሀሳብ ሳይሸራረፍባቸው  የሚያካፍሉበትን መንገድ ለመፍጠር
 • ስፖርቱን ለማሳደግ ይበጃል የሚሏቸው በርካታ ሃሳቦች ላላቸው ነገር ግን ሀሳባቸውን ለመግለጽ መድረኩን ላጡ ባለሞያዎች መድረኩን ለመፍጠር
 • ለኢትዮጵያ ስፖርት እድገት ይበጃሉ የሚባሉ የባለሙያ ምክረ ሀሳቦች በተደራጀ ሁኔታ የሚንሸራሸሩበት ነጻ መድረክ ለመፍጠር
 • ለስፖርቱ ቀጥተኛ ባለ ድርሻ አካላት፣ ለአንባቢዎች እና ለሚዲያ ባለሞያዎች ጥራት ላላቸው መረጃዎች፣ ለተጨማሪ እውቀት እና ለማመሳከሪያነት የሚያገለግል  መድረክ ለመሆን

ፀሀፊዎቹ በምላሹ ምን ሊያገኙ ይችላሉ፡

 • ለኢትዮጵያ ስፖርት እድገት ይበጃል የሚሉትን በእውቀት እና በልምድ የዳበረ ሙያዊ አስተያየታቸውን ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ተደራሽ በሆነ መንገድ የሚያካፍሉበት በጣም ጥሩ መድረክ ያገኛሉ፡፡

ለምን በድረ-ገጽ አማራጭ ፡

 • የድረ-ገጽ የመገናኛ መንገድ ከሚሰጣቸው በርካታ ጥቅሞች በዋነኛነት የሚጠቀሰውን በየትኛውም ጊዜ፣ ቦታ እና ሁኔታ ለምንፈልገው አገልግሎት መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት ስለሚያስችለን፡፡

የልዩ ስፖርት ድረ ገጽ ተደራሾች፡

 • ስፖርት በአሁኑ ወቅት በአለማችን እየተተገበረበት ያለውን መንገድ ልብ ብለን ካስተዋልን ሁሉም የማህበረሰባችን ክፍል የዚህ ድረ-ገጽ ኢላማ ነው፡፡ ምክንያቱም ስፖርት ለቢዮኖች የመኖር መንገድ/ምንጭ ነው፡፡
 • ስፖርት ሁላችንም እንደምንረዳው ከጤና፣ ከመልካም ስብእና ግንባታ ፣ከወንድማማችነት፣ ከስራ ፈጠራ እና  ከበጎ ተፅእኖ ፈጣሪነት ጋር ትስስር አለው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የሀገራትን የጥቃቅን እና ግዙፍ ኢኮኖሚያዊ እድገት አቀጣጣይ  መሳሪያም በመሆን እያገለገለ የሚገኝ ዘርፍ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ድረ-ገጽ ላይ የሚታተሙ ጽሁፎችን የሚያነብ ማንኛውም የማህበረሰባችን ክፍል ለራሱ አላማ መሳካት እንደ ግብዓትነት የሚያገለግሉ ሀሳቦችን እንደሚያገኝ አልጠራጠርም፡፡

የልዩ ስፖርት ድረ-ገጽ የቋንቋ አማራጮች፡

 • ድረ-ገጹ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚዘጋጁ ጽሁፎች እና የድምጽ መሰናዶዎች የሚታተሙበት ይሆናል፡፡

የልዩ ስፖርት ድረ-ገጽ መለያ ቃል፡

“እያንዳንዱ ሀሳብ ዋጋ አለው!”

 • ስለ ልዩ ስፖርት የቪዲዮ ገለፃ