አዲስ አበባ – ሰኔ 23/2011 ዓ.ም

በስኬታማዋ የእግር ኳስ አሰልጣኝ መሰረት ማኒ፡ አስተማሪ የህይወት ታሪክ ዙሪያ የሚያጠነጥን ግለ ታሪክ መጽሀፍ ዛሬ በኢትዮጵያ ሆቴል የአሰልጣኟ ወዳጆች፣ የሙያ አጋሮች እና ሌሎች በርካታ እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ስነ-ስርዓት ተመርቆ ለገበያ ውሏል፡፡

“መሠረት ማኒ፡ የብርታት ተምሳሌት” በሚል ርዕስ በጋዜጠኛ ዘርዓይ እያሱ ተጽፎ፡ በጃጃው አታሚዎች እና ዴቨሎፐርስ ኃላ/የተ/የግ/ማ የታተመው ይህ መጽሀፍ፡ በውስጡ አሰልጣኝ መሠረት ማኒ እዚህ ደረጃ ለመድረስ ያለፈችባቸውን የህይወት ውጣ ውረዶች ለሌሎች አስተማሪ በሆነ መንገድ የሚተርኩ፡ አስር ምዕራፎች እና 200 ገጾች ያሉት ሲሆን፡ መጽሐፉን ከሁሉም የመጽሐፍት መደብሮች በ100 ብር የመሸጫ ዋጋ ማግኘት እንደሚቻልም ተገልጿል፡፡

አሰልጣኝ መሠረት በምርቃቱ ወቅት ከልዩ ስፖርት ጋር በነበራት አጭር ቆይታ”መጽሀፉ እኔ ተጋፍጨ በድል ያለፍኳቸውን ፈተናዎች እና ድሎች የሚተርክ ብቻ ሳይሆን፡  ሌሎች ባለሞያዎች በተለይም ሴቶች ከእኔ መውደቅ እና መነሳት በመማር  ለሀገራችን ስፖርት አዎንታዊ  አስተዋጽኦዎችን ማበርከታቸውን እንዲቀጥሉ ለማነሳሳት እና ከፈተናዎች በኀላ ስኬት እንደሚጠብቃቸው ለማስታወስ እንደሚያግዝም አምናለሁ፡፡ ” ስትል አስተያዬቷን ሰጥታለች፡፡

ከዚህ ቀደም “የአሰልጣኝ ብርሀኑ ግዛው የህይወት ታሪክ” እና “ከሜዳ ውጭ” የተሰኙ መጽሐፍቶችን ለንባብ ያበቃው የመጽሐፉ ፀሀፊ ጋዜጠኛ ዘርዓይ እያሱ በበኩሉ፡ በአጠቃላይ የግለሰቦችን ታሪክ፡ በተለይም ደግሞ እንደ መሠረት አይነት በርካታ የሚነገር ታሪክ ያላቸው ግለሰቦችን ታሪክ ለአንባቢ እንዲመች አድርጎ መጻፍ እጅግ ውስብስብ እና አድካሚ እንደሆነ በመግለጽ  ” አንባቢዎች ከዚህ መጽሐፍ፡ የመሠረት ማኒን ጥንካሬ ፣ የዓላማ ጽናት ፣ ቁርጠኝነት እና ተስፋ አለመቁረጥን እንዲሁም በትንንሽ ስኬቶች አለመርካትን  ይማሩበታል የሚል እምነት አለኝ” ሲል ሃሳቡን አካፍሎናል፡፡

author image

About Liyusport.com

ልዩ ስፖርት ድረ-ገጽ የኢትዮጵያን ስፖርት እና ከባቢውን በመሰረታዊነት ሊለውጡ የሚችሉ የባለሙያ ሃሳቦች: ትችቶች፡ የምርምር ውጤቶች እና ሀተታዊ ጽሁፎች በራሳቸው በባለሞያወቹ ብዕር እና አንደበት ተዘጋጅተው በጽሁፍ እና በድምጽ የሚስተናገዱበት፡ እንዲሁም የምርመራ ጋዜጠኝነትን ጨምሮ ልዩ ልዩ የጋዜጠኝነት ውጤት የሆኑ ፅሁፎች የሚቀርቡበት እና በአይነቱ ልዩ የሆነ የስፖርት ድረ-ገፅ ነው፡፡

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *