የተራዘመው የኢትዮጵያ ቡና እና መቐለ 70 እንደርታ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ በሰላማዊ መንገድ እንደሚከናወን ተገለጸ ፡፡

በኢትዮጵያ ቡና እና መቐለ 70 እንደርታ እግር ኳስ ክለቦች መካከል ተፈጥሮ የነበረው አለመግባባት በአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሸማጋይነት በትላንትናው ዕለት መፍትሔ ማግኘቱ ይታወሳል፡፡

ይህንን አሰመልክቶም ከደቂቃዎች በፊት ሶስቱም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በኢንተርኮንቲኔንታል አዲስ ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል፡፡

በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅትም የአ.አ.እ.ፌ ፕሬዝዳንት ኢንጂ. ኃይለእየሱስ ፍስሃ ይሄ ችግር መፍትሔ እንዲያገኝ የሁለቱ ክለብ አመራሮችን ለውይይት በጋበዟቸው ወቅት ላሳዩት ቀናነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

የሁለቱ ክለብ ሀላፊዎችም በትላንትናው እለት ለአራት ሰዓታት ያክል ከፈጀው ውይይታቸው በኀላ የተስማሙባቸውን ባለ ስድስት ነጥቦች የአቋም መግለጫቸውን በንባብ አቅርበዋል፡፡

ነገ 09:00 በአዲስ አበባ ስቴዲየም የሚከናወነው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ፍጹም ሰላማዊ እንደሚሆን እና የእግር ኳስ መርህ በሚፈቅደው መሰረት ብቻ እንደሚከናወን እንዲሁም የሁለቱ ደጋፊዎችን ክብር የሚመጥን ስነ-ስርዓት የሚታይበት ጨዋታ እንዲሆን ለማድረግ በሁለቱም ደጋፊ ማህበራት በኩል ዝግጅት እየተደረገ እንደሆነ ተገልጿል፡፡

author image

About Liyusport.com

ልዩ ስፖርት ድረ-ገጽ የኢትዮጵያን ስፖርት እና ከባቢውን በመሰረታዊነት ሊለውጡ የሚችሉ የባለሙያ ሃሳቦች: ትችቶች፡ የምርምር ውጤቶች እና ሀተታዊ ጽሁፎች በራሳቸው በባለሞያወቹ ብዕር እና አንደበት ተዘጋጅተው በጽሁፍ እና በድምጽ የሚስተናገዱበት፡ እንዲሁም የምርመራ ጋዜጠኝነትን ጨምሮ ልዩ ልዩ የጋዜጠኝነት ውጤት የሆኑ ፅሁፎች የሚቀርቡበት እና በአይነቱ ልዩ የሆነ የስፖርት ድረ-ገፅ ነው፡፡

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *