የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን በያዝነው ሰኔ ወር አጋማሽ በግብጽ አስተናጋጅነት የሚያካሄደውን 32ኛውን የአፍሪካ ዋንጫ ስኬታማ ለማድረግ በተለያዩ ኮሚቴዎች ውስጥ የሚሳተፉ ሙያተኞችን ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

የ2019ኙን የአፍሪካ ዋንጫ በተለያዩ ዘርፎች የሚያገለግሉ 30 ኮሚቴዎች እና 224 የኮሚቴ አባላት ዝርዝር ይፋ ሲያደረግም፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የውድድሩ የቴክኒክ ጥናት ቡድን አባል ሆነው ተመርጠዋል፡፡

ይህ የቴክኒክ ጥናት ቡድን 15 አባላት ያሉት ሲሆን፡ በዋነኛነት የዉድድሩን ኮከብ ተጫዋች መምረጥ፣ የእያንዳንዱ ጨዋታ ተጽኖ ፈጣሪ ተጫዋችን መለየት፣ የአፍሪካን የእግር ኳስ ደረጃ መገምገም፣ ቴክኒካዊ ጉዳዮችን መገምገም፣ ከውድድሩ የተገኙ አዳዲስ ተሞክሮዎችን በሪፖርት መልክ ማቅረብ ዋና ዋና ተግባራቶቹ መሆናቸው ተገልጿል።

ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ካፍ የሰጣቸውን ሃላፊነት በተመለከተ ”ከብዙ ሀገራት ባለሞያዎች ጋር ያገናኛል ፣ እውቀት እና ልምድ ለመቅሰም እንዲሁም የወዳጅነት ጨዋታዎችን ለማመቻቸትም ይጠቅማል፡፡ ይህንን እድል በማግኘቴም ለእኔ እዚህ ደረጃ መድረስ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ያበረከቱ ሙያተኞችን ፣ የስፖርት ቤተሰቡን ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንን እና ካፍን ከልብ አመሰግናለሁ።” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ከኢንስትራክተር አብርሃም በተጨማሪም ኢትዮጵያውያኑ የጨዋታ ዳኞች ኢንተርናሽናል ዋና ዳኛ ባምላክ ተሰማ እና ኢንተርናሽናል ረዳት ዳኛ ተመስገን ሳሙኤል ውድድሩን እንዲመሩ ከዚህ ቀደም በካፍ መመረጣቸው ይታወሳል፡፡

የመረጃው ምንጭ፡ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ነው፡፡

author image

About Liyusport.com

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *