አለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (IAAF) ከመቶ አመታት በላይ ሲጠቀምበት የነበረውን ስያሜውን እና  አርማውን ቀየረ::

ማህበሩ ትናንት በፈረንሳይ ሞናኮ ባገባደደው የስራ አስፈጻሚ ጉባኤ ስብሰባ ላይ ስፖርቱን በቀላሉ ሊገልጹ እና ሊወክሉ ይችላሉ ባላቸው ስያሜዎች እና አርማወች ነባሮቹን መለያወቹን መተካቱን እና አዳዲሶቹ መለያወችም የፊታችን መስከረም ወር 2012 በዶሃ ኳታር ከሚከናወነው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና መጠናቀቅ በኀላ አገልግሎት ላይ እንደሚዉሉ አስታውቋል፡፡

ማህበሩ ከዚህ ቀደም ይጠቀምበት የነበረውን የአለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የሚለውን ስያሜ ወደ “የአለም አትሌቲክስ” የቀየረ ሲሆን የተቋሙን አላማ እና የወደፊት ራዕይ ያመለክታል ያለውን አዲስ አርማም አዘጋጅቷል፡፡

ከባለፈው አመት መጋቢት ወር ጀምሮ በዚህ ጉዳይ ላይ ከተለያዩ አለም አቀፍ የብራንዲንግ ተቋማት ጋር ሲሰራ መቆየቱን ያስታወቀው ማህበሩ፡ ይህንን የስያሜ እና የአርማ ለውጥ ተግባራዊ ለማድረግ በመተዳደሪያ ደንቡ መሠረት የፊታችን ጥቅምት ወር ላይ በሚኖረው ጠቅላላ ጉባኤ፡ ውሳኔው ድጋፍ አግኝቶ መጽደቅ ይኖርበታል፡፡

የተቋሙ የከዚህ ቀደም አርማ
author image

About Liyusport.com

ልዩ ስፖርት ድረ-ገጽ የኢትዮጵያን ስፖርት እና ከባቢውን በመሰረታዊነት ሊለውጡ የሚችሉ የባለሙያ ሃሳቦች: ትችቶች፡ የምርምር ውጤቶች እና ሀተታዊ ጽሁፎች በራሳቸው በባለሞያወቹ ብዕር እና አንደበት ተዘጋጅተው በጽሁፍ እና በድምጽ የሚስተናገዱበት፡ እንዲሁም የምርመራ ጋዜጠኝነትን ጨምሮ ልዩ ልዩ የጋዜጠኝነት ውጤት የሆኑ ፅሁፎች የሚቀርቡበት እና በአይነቱ ልዩ የሆነ የስፖርት ድረ-ገፅ ነው፡፡

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *