አዳማ ከተማ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የእግር ኳስ ክለቦች የ2011 ዓ.ም የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የየዲቪዚዮኖቹ አሸናፊዎች ሆኑ፡፡

ክለቦቹ ዛሬ በተደረጉ የአመቱ የሴቶች የሊግ ውድድሮች የመዝጊያ ጨዋታዎች ላይ ተጋጣሚዎቻቸውን ላይ ድል በመቀዳጀታቸው ነው የአመቱ አሸናፊዎች መሆናቸውን ያረጋገጡት፡፡

አዳማ ከነማ ዛሬ 09:00 ሰዓት ላይ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚን አስተናግዶ 6ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት በማሸነፍ፡ ከተከታዩና በተመሳሳይ ሰዓት በአዲስ አበባ ስታዲየም የአ.አ ከተማ እግር ኳስ ክለብን 2ለ0 ያሸነፈውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ክለብን በአንድ ነጥብ በመብለጥ በ58 ነጥቦች ለመጀመሪያ ጊዜ የሊጉ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡

አቃቂ ቃሊቲ በበኩሉ ዛሬ ረፋድ በአዲስ አበባ ስቴዲየም በተከናወነ የሴቶች ሁለተኛ ዲቪዚዮን የመዝጊያ ጨዋታ: ሊጉን ሶስተኛ ደረጃ በመያዝ ያጠናቀቀውን ፋሲል ከነማን አስተናግዶ 3ለ2 በሆነ ውጤት በማሸነፍ፡ በ30 ነጥቦች የሊጉ ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል፡፡

በተመሳሳይ ሰዓት ሻሸመኔ ላይ ሻሸመኔ ከነማ በሊጉ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው እና አቃቂ ነጥብ የሚጥል ከሆነ እና ይህን ጨዋታ ማሸነፍ የሚችል ከሆነ የሊጉ ሻምፒዮን የመሆን እድል ከነበረው መቀሌ ሰባ እንደርታ ጋር ያደረጉት ጨዋታ 3ለ2 በሆነ ተመሳሳይ ውጤት በባለሜዳዎቹ አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

የዛሬውን ውጤቱት ተከትሎም አቃቂ ቃሊቲ እና በ26 ነጥቦች ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀው መቀሌ ሰባ እንደርታ የእግር ኳስ ቡድኖች፡ በ2012 ዓ.ም የውድድር ዘመን፡ በዚህ አመት ከአንደኛ ዲቪዚዮን የወረዱትን ኢትዮ ኤሌክትሪክ እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ቡድኖችን በመተካት የሚሳተፉ ይሆናሉ፡፡

author image

About Liyusport.com

ልዩ ስፖርት ድረ-ገጽ የኢትዮጵያን ስፖርት እና ከባቢውን በመሰረታዊነት ሊለውጡ የሚችሉ የባለሙያ ሃሳቦች: ትችቶች፡ የምርምር ውጤቶች እና ሀተታዊ ጽሁፎች በራሳቸው በባለሞያወቹ ብዕር እና አንደበት ተዘጋጅተው በጽሁፍ እና በድምጽ የሚስተናገዱበት፡ እንዲሁም የምርመራ ጋዜጠኝነትን ጨምሮ ልዩ ልዩ የጋዜጠኝነት ውጤት የሆኑ ፅሁፎች የሚቀርቡበት እና በአይነቱ ልዩ የሆነ የስፖርት ድረ-ገፅ ነው፡፡

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *