ኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ የቀድሞውን የቡድኑን ውጤታማ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች፡ ካሳዬ አራጌን ከሚቀጥለው የውድድር ዘመን ጀምሮ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ አድርጎ መምረጡንአስታወቀ፡፡

ክለቡ በዛሬው ዕለት በፌስቡክ ገጹ ባወጣው መግለጫ መሠረት ፡ የክለቡን የከዚህ ቀደም የአጨዋወት ባህል በሚገባ እንደሚረዳ እምነት የተጣለበት አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ከ2012 ዓ.ም የውድድር ዘመን ጀምሮ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ በመሆን እንዲያገለግል፡ ክለቡ አዲስ ያዋቀረው የቴክኒክ ኮሚቴ ምርጫን መሰረት አድርጎ የክለቡ ስራ አመራር ቦርድ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

ከዚህ ቀደም የክለቡ አሰልጣኝ የነበረው ካሳዬ፡ አሁን ከሚኖርባት ሀገረ አሜሪካ በቶሎ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት በግል ጉዳዮች ዙሪያ ከክለቡ ጋር ተጨማሪ ድርድር እንደሚያደርግም ይጠበቃል፡፡

በግል ጉዳዮች ዙሪያ የሚደረገው ድርድር በቶሎ የሚጠናቀቅ ከሆነ፡ የዘንድሮው የሊግ ውድድር ከማለቁ በፊት በሚደረጉ የመጨረሻ ሳምንታት ጨዋታዎች ላይ በአካል በመታደም ለቀጣይ የውደድር ዘመን የቡድኑ አካል ለማድረግ የሚፈልጋቸውን ተጫዋቾች የመመልመል ስራ እንደሚጀምርም ተነግሯል፡፡

ይሁንና ክለቡ ለአሰልጣኙ ያቀረበው የኮንትራት ዘመን ርዝማኔ እና በፋይናንስ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫው ምንም ያለው ነገር የለም፡፡

መረጃ፡ የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ

author image

About Liyusport.com

ልዩ ስፖርት ድረ-ገጽ የኢትዮጵያን ስፖርት እና ከባቢውን በመሰረታዊነት ሊለውጡ የሚችሉ የባለሙያ ሃሳቦች: ትችቶች፡ የምርምር ውጤቶች እና ሀተታዊ ጽሁፎች በራሳቸው በባለሞያወቹ ብዕር እና አንደበት ተዘጋጅተው በጽሁፍ እና በድምጽ የሚስተናገዱበት፡ እንዲሁም የምርመራ ጋዜጠኝነትን ጨምሮ ልዩ ልዩ የጋዜጠኝነት ውጤት የሆኑ ፅሁፎች የሚቀርቡበት እና በአይነቱ ልዩ የሆነ የስፖርት ድረ-ገፅ ነው፡፡

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *