በብራዚል ሪዮ ዲ ጄኔሮ በተከናወነው የ2016ቱ የኦሊምፒክ ጨዋታዎች፡ የሴቶች ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያኑ ማሬ ዲባባ እና ትርፌ ጸጋዬ 3ኛ እና 4ኛ ደረጃዎችን በመያዝ ማጠናቀቃቸው ይታወሳል፡፡

ይሁንና ከሶስት አመታት በፊት በተከናወነው ውድድር 1ኛ እና 2ኛ በመሆን በቀዳሚነት ያጠናቀቁት፡ ኬንያዊቷ ጀሚማ ሱምጎግ፡ ከሁለት አመታት በፊት እና ባህሬናዊቷ ኢዩኒስ ኪርዋ ደግሞ ከሁለት ቀናት በፊት፡ EPO የተሰኘ ለስፖርት የተከለከለ አበረታች መድሀኒት ተጠቅመው በመገኘታቸው፡ ሱምጎግ የ8 አመታት ኪርዋ ደግሞ በጊዜያዊነት በIAAF የውድድር እገዳ ቅጣት ተጥሎባቸዋል፡፡ ይህን ተከትሎም የሪዮ ኦሊምፒክ የሴቶች ማራቶን ውድድርን የምንጊዜም አስቀያሚው የኦሊምፒክ ውድድር በማለት እየገለጹት ይገኛሉ፡፡
ነገር ግን አትሌቶቹ በተጨማሪ ምርመራዎች አበረታች መድሀኒቱን ከውድድሩ አሰቀድሞ መውሰዳቸው እስካልተረጋገጠ ድረስ፡ የኦሊምፒክ ባለድልነታቸውን ለጊዜው እንደማይነጠቁ ታውቋል፡፡

ሆኖም ግን፡ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቷ ሱምጎግ አበረታች መድሀኒቱን እንደተጠቀመች በምርመራ የተረጋገጠው ከኦሎምፒክ ድሏ ስድስት ወራት በኀላ መሆኑ ጉዳዩን እጅግ አጠራጣሪ አድርጎታል፡፡

ምናልባትም በተጨማሪ ምርመራዎች ምክንያት ሁለቱ አትሌቶች ከኦሎምፒክ ውድድሩ አስቀድሞ አበረታች ንጥረ ነገሩን እንደተጠቀሙ ከተረጋገጠ፡ ኢትዮጵያውያኑ ማሬ ዲባባ እና ትርፌ ጸጋዬ ደረጃቸው ወደ ወርቅ እና ብር ከፍ ሊል የሚችልበት እድል ተፈጥሯል፡፡

ይህ እንዲሆን ግን ቅድሚያ IAAF ለ International Olympic Committe ጉዳዩን አቅርቦ ማሳመን እና ማስወሰን ይኖርበታል፡፡ ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሺን እና ብሔራዊ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ጉዳዩን አጥብቀው በመያዝ ተጨማሪ ምርመራዎች እንዲደረጉ ጥያቄ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

author image

About Liyusport.com

ልዩ ስፖርት ድረ-ገጽ የኢትዮጵያን ስፖርት እና ከባቢውን በመሰረታዊነት ሊለውጡ የሚችሉ የባለሙያ ሃሳቦች: ትችቶች፡ የምርምር ውጤቶች እና ሀተታዊ ጽሁፎች በራሳቸው በባለሞያወቹ ብዕር እና አንደበት ተዘጋጅተው በጽሁፍ እና በድምጽ የሚስተናገዱበት፡ እንዲሁም የምርመራ ጋዜጠኝነትን ጨምሮ ልዩ ልዩ የጋዜጠኝነት ውጤት የሆኑ ፅሁፎች የሚቀርቡበት እና በአይነቱ ልዩ የሆነ የስፖርት ድረ-ገፅ ነው፡፡

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *