የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የ2020 ቻን የአፍሪካ ዋንጫ እግር ኳስ ውድድርን ለማዘጋጀት ያስፈልጋል የተባለውን የ300ሚ ብር በጀት እና ሌሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ያሟላ “የውድድር ማዘጋጃ ሰነድ” አዘጋጅቶ ለመንግስት ቢያቀርብም እስካሁን ድረስ ከመንግሥት በኩል ምንም አይነት ምላሽ አለማግኘቱን ዛሬ ረፋድ በአዲስ አበባ ስታዲየም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ ይህንን ውድድር ለማዘጋጀት ብቁ ናቸው  ያለቻቸውን 6 ስታዲየሞች (አዲስ አበባ: ሀዋሳ፡ ባህር ዳር፡ መቀሌ፡ ድሬዳዋ እና ሀረር) ፡ 12 የልምምድ ቦታዎችን፡ 20 ሆቴሎች እና 5 ኤርፖርቶችን ያጠቃለሉ የመሠረተ ልማቶቿን፡  ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሺን  (ካፍ) ልዑክ ከአንዴም ሁለቴ ያስገመገመች ቢሆንም ከሚጠበቅባት መስፈርት አንጻር ያሟላችው እጂግ ጥቂቱን በመሆኑ ውድድሩን እንዳታዘጋጅ እንዳደረጋት ተገልጿል፡፡ ለዚህም ደግም በዋነኛነት መንግስት ውድድሩ በሚጠይቀው ልክ ቁርጠኛ አለመሆኑ ነው ተብሏል፡፡

የካፍ ገምጋሚ ቡድን ባደረገው ማጣራት መሰረት፡ ሁሉም ስታዲየሞቻችን በግንባታ ላይ ያሉ እና የውድድሩ ጊዜ በመቅረቡ ምክንያት የመጠናቀቅ እድላቸው ጠባብ በመሆኑ፡ የመሰረት ልማት አስተዳደር ስርአት እና ባለሞያ እጥረት በመኖሩ፡ የመጫወቻ ሜዳዎቹ ፈጽሞ ደረጃቸውን ያልጠበቁ፡ የመለማመጃ ሜዳዎች በተፈላጊው ደረጃ ላይ የማይገኙ በመሆናቸው እና በተገነቡት ስታዲየሞቻችን ላይ መሰረታዊ የዲዛይን ለውጥ  እስከማስደረግ የሚደርሱ ክፍተቶች በመኖራቸው ምክንያት፡ ኢትዮጵያ በዋናነት ውድድሩን ለማዘጋጀት እንዳትችል እንዳደረጋት ገልጸው፡ በሆቴል እና የአየር ትራንስፖርት አቅርቦት በኩል ግን ኢትዮጵያ ለውድድሩ ዝግጁ መሆኗን አስታውቀዋል፡፡

ፌዴሬሽኑ አብዛኛዎቹ ስታዲየሞች በክልል መንግስታት ባለቤትነት የሚተዳደሩ በመሆኑ፡ በተደጋጋሚ ጊዜ በካፍ መሠረተ ልማቶቹ እንዲያስተካከሉ የተባሉትን ነገሮች እንዲያሻሽሉ ጥረት ቢያደርግም እንዳልተሳካለት ገልጿል፡፡

በተጨማሪም አሁን ያሉ ነገሮችን በሚገባ በመገምገም እና በማሻሻል ኢትዮጵያ የቻን 2022 እና የ2025 የአፍሪካ ዋንጫ ውድድሮችን ለማዘጋጀት ጥረት እንደምታደርግ  እና የቻን 2022 ውድድርን በተመለከተም በካፍ በኩል መልካም አተያይ እንዳለ፡ የፌዴሬሽኑ የክለብ ፈቃድ ሀላፊ አቶ ተድላ ዳኛቸው በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ አስታውቀዋል፡፡

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You Might Also Like...