የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እና የጀርመኑ ባየር ሙኒክ እግር ኳስ ክለብ ለሶስት አመታት የሚዘለቅ የእግር ኳስ ልማት ትብብር ስምምነት ፈጸሙ

በስምምነቱ መሰረት ክለቡ የ17 አመት በታች ታዳጊዎች ማሰልጠኛ ማእከልን በኢትዮጵያ የሚከፍት ሲሆን፡ በተጨማሪም ኢትዮጵያውያን የቴክኒክ እና የአስተዳደር ባለሙያወች ተጨማሪ ስልጠናወችን በኢትዮጵያ እና በጀርመን እንዲያገኙ የሚደረግ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ክለቡ ኢትዮጵያውያን እንደ ጀርመኖች እንዲጫወቱ ሳይሆን ያላቸውን ጥሩ ጎን የበለጠ ለማበልጸግ መስራት ፍላጎቱ እንደሆነም ገልጿል፡፡

የስምምነቱን መጀመር አስመልክቶ ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሸነር እና የክለቡ ተወካዮች በተገኙበት በስምንት የአዲስ አበባ ታዳጊ ቡድኖች መካከል የእግር ውድድር ተካሂዷል፡፡

ክለቡ ባለፉት ቅርብ አመታት ውስጥ በቻይና፡ ሲንጋፖር፡ ታይላንድ፡ ጃፓን እና አሜሪካ መሰል የታዳጊዎች ማሰልጠኛ ፕሮጀክቶችን የከፈተ ሲሆን በኢትዮጵያ ሊከፍተው ያሰበው ማሰልጠኛ ማዕከል ደግሞ በአፍሪካ የመጀመሪያው እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡

author image

About Liyusport.com

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

You Might Also Like...