አዲስ አበባ ሀምሌ 30/2014 ዓ.ም – በካሊ፡ ኮሎምቢያ ላለፉት ስድስት ቀናት ለ19ኛ ጊዜ ሲካሄድ በሰነበተው የ2022 የአለም ከ20አመት በታች የአትሌቲክስ ሻምፒዮና፡ ኢትዮጵያ በአስደናቂ ውጤት ውድድሩን ፈጽማለች።

ኢትዮጵያ በተለይም ዛሬ ሌሊት በተከናወኑ የመጨረሻው ዕለት የፍጻሜ ውድድሮች፡ በ800ሜ ወንዶች በአትሌት ኤርሚያስ ግርማ ወርቅ፣ በ3000ሜ መሰናክል ወንዶች በሳሙኤል ዱጉና እና ሳሙኤል ፍሬው ወርቅ እና ብር፣ በ5000ሜ ሴቶች በመዲና ኢሳ እና መልክናት ውዱ በተመሳሳይ ወርቅ እና ብር እንዲሁም በ1500ሜ ሴቶች ደግሞ በአትሌት ብርቄ ሀየሎም (4:04.27) የሻምፒዮናውን ክብረ-ወሰን በማሻሻል ጭምር የወርቅ ሜዳሊያወችን ማሸነፍ ችላለች።

ከፍጻሜው ቀን አስቀድሞ በነበሩ ሌሎች ውድድሮች፡ ኢትዮጵያ፡ በ5000 እና 3000ሜ ወንዶች በአዲሱ ይሁኔ እኔ መልኬነህ አዘዝ የወርቅ፣ በ3000ሜ መሠናክል ሴቶች በሲምቦ አለማየሁ፣ በ1500ሜ ወንዶች በኤርሚያስ ግርማ እና በ3000ሜ ሴቶች በፅዮን አበበ የብር ሜዳሊያወችን ያሸነፈች ሲሆን፣ በተጨማሪም በሴቶች 3000ሜ መሰናክል በአትሌት መሰረት የሻነህ የነሀስ ሜዳልያ ማግኘቷ ይታወቃል።

ይህንን ውጤት ተከትሎም ኢትዮጵያ በሜዳሊያ ሰንጠረዡ በ ስድስት ወርቅ፣ አምስት ብር እና አንድ የነሀስ በድምሩ በ12 ሜዳሊያዎች፡ ከአሜሪካ እና ጃማይካ በመቀጠል ከአለም ሶስተኛ ከአፍሪካ ደግሞ በቀዳሚነት ውድድሯን ፈጽማለች።

በ19 ወጣት አትሌቶች እና በ10 የውድድር አይነቶቾ ተሳትፎ ብቻ የተገኘው ይህ አስደናቂ ውጤት፡ በሻምፒዮናው ታሪክ ለኢትዮጵያ የምንጊዜም ከፍተኛው ሆኖ ተመዝግቧል።

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *