ከአመት በፊት አለም አቀፍ ደረጃውን እንዲያሟላ እና ውድድሮችን እንዳያዘጋጅ እድሳቱ የተጀመረለት የአዲስ አበባ ብሔራዊ ስታዲየም ወደ መጨረሻው የስራ ምዕራፍ መቃረቡ ተገልጿል።

የእስካሁኑ የእድሳት ክንውን ካፍ የሰጣቸውን አስተያየቶች መሠረት አድርጎ እየተሰራ እንደሆነ የተነገረ ሲሆን በዚህም መሰረት እስካሁን ድረስ በዋናነት የመጫወቻ ሜዳው፣ የመልበሻና የመታጠቢያ ክፍሎች፣ የተመልካቾች መፀዳጃ፣ የሚዲያ ክፍሎች፣ የክብር እንግዶች ክፍል እና የኤሌክትሪክ እና የሳኒተሪ ስራዎችን በማካተት እየተሰራ ይገኛል።

በትላንትናው እለትም የባህልና ስፖርት ሚኒስትሩ አቶ ቀጄላ መርዳሳ በአዲስ አበባ ስታዲየም በመገኘት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ለውድድር ዝግጁ እንደሚሆን የሚጠበቀውን የመጫወቻ ሜዳ ሳር የማልበስ መርሃ ግብር አስጀምረዋል።

ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት እንደገለፁት የስታዲየሙን የእድሳት ስራ በተቀመጠለት የጊዜ ገደብ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ዝግጁ ለማድረግ ርብርብ እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ስቴዲየሙ በእቅዱ መሰረት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እድሳቱ ከተጠናቀቀ እና አለምአቀፍ መመዘኛወችን የሚያሟላ ከሆነ፡በመጪው መስከረም ኢትዮጵያ ከጊኒ የሚያደርጉት የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ ሶስተኛ የምድብ ማጣሪያ ጨዋታ በአዲስ አበባ ስታዲየም የሚካሄድ ይሆናል።

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *