ኢንተርናሽናል አርቢትር ሊዲያ ታፈሰ፡ በሞሮኮ አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የሴቶች የአፍሪካ ዋንጫ በዳኝነት መመረጧን የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፍዴሬሽን ይፋ አድርጓል።

ኢትዮጵያዊቷ ስኬታማ የእግር ኳስ ዳኛ፡ ከሰኔ 25/ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ሳምንታት በሚከናወነው እና 12 ብሔራዊ ቡድኖችን በሚያሳትፈው ትልቁ የሴቶች አህጉር አቀፍ ውድድር፡ በሀላፊነት ስትመረጥ ይህ ለተከታታይ አምስተኛ ጊዜዋ ነው።

እ.ኤ.አ በ2006 የመጀመሪያ ኢንተርናሽናል ጨዋታዋን በአቡጃ፡ናይጄሪያ እና ላይቤሪያ ያደረጉትን ጨዋታ በመዳኘት የጀመረችው ሊድያ በ2007 እና 2011 በመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ላይም ሀገሯን ወክላለች፡፡

ሊዲያ ከአፍሪካ ዋንጫ በተጨማሪ በፊፋ ከ17 ዓመት በታች ውድድር 2016፣ ከ20 ዓመት በታች በ2018 በዳኝነት ሙያዋ በብቃት ተልዕኮዋን ተወጥታለች። በ2015 እና 2019 ደግሞ በታላቁ የሴቶች ዓለም ዋንጫ መድረክ ውድድሮችን መርታለች፡፡

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *