በሄንግሎ፡ ሆላንድ በተካሄደ የ10,000ሜ የአለም ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ማጣሪያ አትሌት ሰለሞን ባረጋ እና ለተሰንበት ግደይ በቀዳሚነት ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

የፊታችን ሐምሌ ወር በአሜሪካን ሀገር በሚካሄደው የኦሬገኑ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን በርቀቱ የሚወክሉ አትሌቶችን ለመምረጥ በተካሄደው የማጣሪያ ውድድር፡ አትሌት ታደሰ ወርቁ እና በሪሁ አረጋዊ በወንዶቹ ምድብ ሰለሞንን ተከታትለው በመግባት ቀሪዎቹን የውክልና ቦታወች ማግኘት ችለዋል።

የርቀቱ የአለም ሻምፒዮና የብር ሜዳሊያ አሸናፊው አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ አራተኛ ሆኖ በማጠናቀቁ ምክንያት በውደድሩ የማንመለከተው ይሆናል።

በሴቶቹ ምድብ በተከናወነው ማጣሪያ ስኮትላንዳዊቷ ኤሊሽ ማክሎጋን ውድድሩን ብታሸንፍም፡ በሁለተኛነት ያጠናቀቀችው ለተሰንበት ግደይ የኢትዮጵያ ማጣሪያን በበላይነት በማጠናቀቅ የኦሬገኑን ትኬት ቆርጣለች።

እጅጋየሁ ታዬ እና ቦሰና ሙላት ቀሪዎቹን ቦታዎች በመያዝ ለአለም ሻምፒዮናው ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። በማጣሪያው ላይ የአለም እና የኦሊምፒክ ሻምፒዮኗ አልማዝ አያና ከረጅም ጊዜ በኋላ ወደ ትራክ ውድድር ተመልሳ ስድስተኛ ደረጃን ይዛ ብታጠናቅቅም ወደ ኦሬገን ለመሄድ ግን በቂ አልነበረም።

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *