የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በማላዊ ቆይታ ከወጪው በላይ ትርፍ አስመዝግቧል

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የሜዳውን ጨዋታ ለማድረግ በማላዊ ባደረገው ቆይታ ግብፅ ላይ ካስመዘገበው ጣፋጭ ድል በተጨማሪ ከወጪው በላይ ገቢ በማስገባት ትርፍ ማስመዝገብ ችሏል ።

ቡድናችን ከግብፅ ጋር በቢንጉ ስታዲየም ባደረገው ጨዋታ 20,000 ተመልካች እንዲታደሙ ተፈቅዶ የነበረ ሲሆን በዚህም 30 የቴሌቪዥን እና 120 የሬዲዮ ማስታወቂያዎችን በማስነገር እና የከተማ ውስጥ ማስታወቂያዎችን በመስራት ትኬቶቹን በመሸጥ 54 ሺህ ዶላር ገቢ ተገኝቷል ።

በማላዊ ጨዋታውን ለማዘጋጀት ማለትም ለሜዳ ኪራይ ፣ ለተሽከርካሪዎች ፣ ለአስተዳደር ወጪ ፣ ለፖሊስ እና የፀጥታ ሃይል ፣ ለህክምና አገልግሎት ፣ ለስታዲየም መብራት ክፍያ ፣ ለማርኬቲንግ ከወጣው 36,000 ዶላር አንፃር ጥሩ የሚባል ገቢ ማግኘት ተችሏል ። ከዚህ ገቢ ላይም ለማላዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከገቢ ላይ ድርሻ 5,340 ዶላር ክፍያ ተፈፅሟል ።

ከቲኬት ሽያጭ በተጨማሪ በሜዳ ዙሪያ 22 የማስታወቂያ ሰሌዳዎች የተቀመጡ ሲሆን ከዚህም በአጠቃላይ 55,000 ዶላር ገቢ ተገኝቷል ።

በዚህም መሰረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከግብፅ ጋር ባደረገው ጨዋታ 68 ሺህ ዶላር የተጣራ ገቢ ማግኘት ችሏል ።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *