የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በ2023ቱ የኮትዲቯሩ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የግብጽ አቻውን ከአሳማኝ የጨዋታ ብልጫ ጋር ሁለት ለዜሮ በሆነ ውጤት አሸንፏል።

ብሔራዊ ቡድኑ በሀገር ውስጥ አለምአቀፍ ውድድሮችን የሚያስተናግድ አንድም ስቴዲየም ባለመኖሩ ምክንያት የማጣሪያ ጨዋታዎቹን ከሀገር ውጭ እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን፣ ይህንን ጨዋታም ያደረገው ሊሎንግዌ፡ ማላዊ ላይ ነው።

ለአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ቡድን የማሸነፊያ ጎሎቹን ዳዋ ሆቴሳ እና ሽመልስ በቀለ ከእረፍት በፊት ሲያስቆጥሩ፡ ድሉን ተከትሎ ኢትዮጵያ ከሁለት ጨዋታዎች በኋለ ምድብ አራትን በሶስት ነጥብ እና በተሻለ የጎል ክፍያ እየመራች ትገኛለች።

ዋልያዎቹ በፈርዖኖቹ ላይ ያስመዘገቡት ይህ ድል ከ31 አመታት በኋላ የተገኘ ሲሆን፡ ቡድኑ በዕለቱ ካሳየው አስደማሚ ብቃት እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ባለው ወቅታዊ ፖለቲካዊ ሁኔታ ድሉን የበለጠ ጣፋጭ እንዳደረገላቸው ብዙዎች ሀሳባቸውን ገልጸዋል።

በውጤቱ የተደሰተው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴም፡ ለብሔራዊ ቡድኑ አባላት የሁለት ሚሊዮን ብር የማበረታቻ ሽልማት አበርክቷል።

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *