በ18ኛው የአለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ውድድሩን በበላይነት ላጠናቀቁት ጀግኖች አትሌቶች የጀግና አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

የኢፌዲሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስትር ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ይፋዊ የአቀባበል ስነ ስርዓት መርሃግብር መሰረት፡ አትሌቶቹ ዛሬ ማለዳ ቦሌ አለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፡ ሚንስትሩ የተከበሩ አቶ ቀጀላ መርዳሳ እና የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ ሌሎች የስራ ሀላፊዎች በስፍራው በመገኘት የጉንጉን አበባ ስጦታ በማበርከት ተቀብለዋቸዋል።

በአራት ወርቅ፣ ሶስት ብር እና ሁለት የነሀስ ሜዳሊያዎች ከአለም አንደኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው የአትሌቲክስ ልዑክ፡ ከቦሌ አየር ማረፊያ በመነሳት በሞተረኛ ታጅቦ ሸራተን አዲስ ሆቴል ከደረሰ በኋላ የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶለታል።

ፌዴሬሽኑ ለቡድኑ አመራሮቾ ብር 160,000.00፣ ለአሰልጣኞች ብር 305,000.00 እንዲሁም ለአትሌቶች ብር 305,000.00 በአጠቃላይ የብር 770,000.00 የገንዘብ ሽልማት አበርክቷል።

📸 Ethiolivescore

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *