ኢትዮጵያ ከመጋቢት 9-11/2014 ዓ.ም በቤልግሬድ የተካሄደውን 18ኛውን የአለም አትሌቲኪስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በአንደኛነት አጠናቀቀች።

ኢትዮጵያ: አትሌት ለምለም ሀይሉ እና ጉደፍ ፀጋይ በሴቶች 3000ሜ እና 1500ሜ፣ ሰለሞን ባረጋ እና ሳሙኤል ተፈራ በወንዶች ተመሳሳይ ርቀቶች ወርቅ፤ አትሌት ለሜቻ ግርማ (3000ሜ ወንዶች)፣ ፍሬወይኒ ሀይሉ(800ሜ) እና አክሱማዊት እምባዬ(1500ሜ) ሴቶች ብር እንዲሁም አትሌት እጅጋየሁ ታዬ (3000ሜ) እና ሒሩት መሸሻ (1500ሜ) በሴቶች ነሀስ፡ ባስመዘገቧቸው አጠቃላይ ዘጠኝ ሜዳሊያወች አማካኝነት በውድድሩ ከተሳተፉ 136 ሀገራት መካከል በቀዳሚነት ለማጠናቀቅ ችላለች።

14 ተወዳዳሪ አትሌቶችን በመያዝ ወደ ሰርቢያ የተጓዘችው ኢትዮጵያ፣ ዘጠኝ አትሌቷቿ የሜዳሊያ ባለቤቶች ሆነውላታል። የ1500ሜ ሻምፒዮኖቹ አትሌት ጉደፍ ፀጋይ (3:57.19) እና ሳሙኤል ተፈራ (3:32.77) የውድድሩን ክብረወሰን በማሻሻል ጭምር ሲያሸንፉ: በ1500ሜ ሴቶች የተመዘገበው ድል ደግሞ ኢትዮጵያን በሻምፒዮናው ታሪክ ሶስቱንም ሜዳሊያዎች ጠራርጋ ያሸነፈች የመጀመሪያዋ ሀገር በመሆን ሌላ አስደናቂ ታሪክ እንድታስመዘግብ አስችሏታል።

በ2022ቱ የአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና የተመዘገበው ይህ ስኬት በውድድሩ ታሪክ ለኢትዮጵያም ሆነ ለአፍሪካ የምንጊዜም ከፍተኛው ውጤት ነው።

©ልዩስፖርት

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *