በሰርቢያ: ቤልግሬድ እየተካሄደ በሚገኘው 18ኛው የዓለም የቤት ውስጥ የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በሴቶች የ1500ሜትር ውድድር ሁሉንም ሜዳልያዎች ጠራርጋ አሸንፋለች።

የወቅቱ የዓለማችን የርቀቱ ምርጥ አትሌት ጉደፍ ፀጋዬ 3:57.20 በመግባት የውድድሩን ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭምር የወርቅ ሜዳሊያውን ስታሸንፍ: የሀገሯ ልጆች የሆኑት አክሱማይት እምባዬ (4:02.29) እና ሒሩት መሸሻ (4:03.39) ደግሞ ተከታትለው በመግባት የብር እና የነሀስ ሜዳሊያዎችን ለሀገራቸው አምጥተዋል።

ይህንን ድል ተከትሎም ኢትዮጵያ በዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ታሪክ በአንድ ርቀት ሶስቱንም ሜዳሊያዎች ጠራርጋ ያሸነፈች የመጀመሪያዋ ሀገር በመሆን አዲስ ታሪክ ሰርታለች።

(Photo by Alex Pantling/Getty Images)

ኢትዮጵያ በዚህ ሻምፒዮና ከዛሬ በፊት በሴቶች የ3000ሜ ፉክክር በለምለም ሀይሉ እና እጅጋየሁ ታዬ ያሸነፈቻቸውን የወርቅ እና የነሀስ ሜዳሊያዎችን ጨምሮ በድምሩ በ5 ሜዳሊያዎች የአጠቃላይ የሜዳሊያ ሰንጠረዡን እየመራች ትገኛለች።

ሻምፒዮናው ዛሬ ፍጻሜውን የሚያገኝ ሲሆን ማጣሪያቸውን በአስደናቂ ብቃት ያለፉት ኢትዮጵያውያን አትሌቶችም ለተጫማሪ ድል ይጠበቃሉ።

በዚህም መሰረት:
ቀን 8:05 – በወንዶች 3000ሜ ፍጻሜ
ለሜቻ ግርማ እና ሰለሞን ባረጋ

ምሽት 2:05 – በሴቶች 800ሜ ፍጻሜ
ሀብታም አለሙ እና ፍሬወይኒ ሀይሉ

ምሽት 2:35 – በወንዶች 1500ሜ ፍጻሜ
ሳሙኤል ተፈራ እና ታደሰ ለሚ: ውድድሮቻቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል።

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *