የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2014 የመጀመሪያ ዙር ቁጥራዊ መረጃዎች

ጨዋታዎች

– 120 ጨዋታዎች በሁለት ከተሞች (72 በሀዋሳ እና 48 በድሬደዋ) ተካሂደዋል።

– ከጨዋታዎቹ 81 በመሸናነፍ 39ኙ በአቻ የተጠናቀቁ ናቸው።

ጎል

– በ120 ጨዋታዎች 238 ጎሎች የተመዘገቡ ሲሆን፣ 198 በጨዋታ፣ 35 በፍፁም ቅጣት ምት እና 5 በራስ ላይ ሲቆጠሩ፣ ሀዋሳ ላይ 131 እንዲሁም በድሬደዋ ደግሞ 107 ጎሎች ተመዝግበዋል።

ተጫዋቾች

– በ16ቱ የፕሪሚየር ተሳታፊ ክለቦች በሊጉ 482 ተጫዋቾች ተመዝገበዋል።

– ከአጠቃላይ ቁጥሩ 107 ተጫዋቾች ከ23 አመት በታች ናቸው።

– 32 የውጭ ሀገር ተጫዋቾች ከ11 የአፍሪካ ሀገራት በሊጉ ሲሳተፉ ጋና በ13፣ ኬንያ 3፣  ናይጄሪያ 3፣ አይቬሪኮስት 2፣ ኤርትራ 2፣ ማሊ 2፣ ቶጎ 2፣ ኡጋንዳ 2፣ ቡረኪናፋሶ 1፣ ካሜሮን 1 እና ጊኒ 1 ተጫዋቾች ተወክለዋል።

ካርዶች

– በ15 ሳምንታት የሊጉ ጉዞ በአጠቃላይ 544 ካርዶች ሲመዘዙ: ከነዚህ ውስጥ 533ቱ ቢጫ (19 በሁለት ቢጫ) ሲሆኑ 11ዱ ደግሞ በቀጥታ የተመዘዙ ቀይ ካርዶች ናቸው።

የካርድ ስርጭቱን በመጫወቻ ዲፓርትመንቶች ከፋፍለን ስንመለከተው ደግሞ፣ 210 ተከላካይ፣ 148 አማካይ፣ 119 አጥቂ እና 45 ግብ ጠባቂዎች ሲመለከቱ የተቀሩት 11 ደግሞ  የቴክኒካል ስታፎች ናቸው።

– በሀዋሳው ውድድር ላይ 316 ቢጫ እና 7 ቀይ ካርዶች የተመዘዙ ሲሆን ድሬደዋ ላይ ደግሞ 217 ቢጫ እና 4 ቀይ ካርዶች ተመዝግበዋል።

– 10 ተጫዋቾች በ5 ቢጫ ካርድ ቅጣት አንድ ጨዋታ የተቀጡ ናቸው።

ምንጭ: የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *