የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከጀርመኑ የልማት ተቋም ጂአይዜድ (GIZ) ጋር በፌዴሬሽኑ ሥር የሚገኘው የካፍ የልህቀት ማዕከል የመጫወቻ እና ልምምድ ሜዳን ደረጃ ለማሻሻል እንዲሁም አዲስ ተጨማሪ ሜዳ ለመሥራት የሚያስችል የ10 ሚልየን ብር ስምምነት በትናንትናው ዕለት ተፈራርመዋል።

በስምምነቱ መሠረት ጂአይዜድ በካፍ የልህቀት ማዕከል የሚገኘውን የመጫወቻ ሜዳ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የመልሶ ግንባታ ሥራ የሚያከናውን ሲሆን አንድ ተጨማሪ አዲስ ሜዳ ደግሞ የሚገነባ ይሆናል። ከመልሶ እና አዲስ ግንባታው በተጨማሪ ለጥገና እና እንክብካቤ ሠራተኞች የሚሰጠው ስልጠናም የስምምነቱ አካል ነው።

ምንጭ: የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *