አትሌት ሙክታር ኢድሪስ በማህበራዊ ሚዲያው ዜግነቱን ወደ ቱርክ ቀይሯል በሚል ስለሚናፈሰው መረጃ ከልዩ ስፖርት ጋር አጠር ያለ ቆይታ አድርጓል።

የሁለት ጊዜ የ5000ሜ የአለም ሻምፒዮኑ አትሌት ሙክታር፡ መረጃውን ከማህበራዊ ሚዲያ ተመለከትን ባሉ ሰዎች ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ መስማቱን ገልጾ፤

“ምንም እንኳን ከአስር አመታት በፊት፡ ገና ወደ አትሌቲክሱ አለም ስቀላቀል፣ በተደጋጋሚ የውድድር እና የማኔጅመንት እጦት ምክንያት፡ እንደማንኛውም አትሌት፡ የተሻሉ ዕድሎችን ለማግኘት ስል አንዳንድ እንቅሰቃሴዎችን ባደርግም፡ ምንም ነገር በሌለበት በዚህ ሰዓት ይሄ ነገር እንደ አዲስ መወራቱ አስገርሞኛል።

አሁን በጥሩ ሁኔታ: ሀገሬን በተከታታይ ለሶስተኛ ጊዜ በአለም ሻምፒዮና ባለድል ለማድረግ ጠንካራ ዝግጅት ላይ እገኛለሁ።” ሲል አስተያዬቱን ሰጥቷል።

©ልዩስፖርት

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *