ሀዋሳ ጥር 06/2014 ዓ.ም – የሀዋሳ ስቴዲየምን ለማጠናቀቅ 2.1 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ተባለ። የኢፌዲሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚንስትር የተከበሩ አቶ ቀጀለ መርዳሳ እና ሚንስትር ዲኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት፡ ከሲዳማ ክልል ባህልና ስፖርት ቢሮ ሀላፊዎች ጋር በመሆን ስቴዲየሙ አሁን የሚገኝበትን ደረጃ ጎብኝተዋል።

ግንባታው በ2005 ዓ.ም የተጀመረው የሀዋሳ ስቴዲየም እስካሁን ድረስ 800ሚሊዮን ብር ለግንባታ ወጪ የተደረገበት ሲሆን በፊፋ እና ካፍ መስፈርት አለምአቀፍ ውድድሮች እንዲያዘጋጅ አድርጎ ለማጠናቀቅ ተጨማሪ የ2.1 ቢሊየን ብር በጀት እንደሚያስፈልገውም ተገልጿል።

ስቴዲየሙ አገልግሎት መስጠት እንዲጀምር ለማድረግ በዋናነት የመጫወቻ ሜዳ፣ የመልበሻ ክፍል፣ የክቡር ትሪቡን እና የመለማመጃ ሜዳ ችግሮቹን መቅረፍ እንደሚኖርበት የካፍ ባለሞያዎች ሀሳብ አቅርበዋል።

ሚንስትሩ ሀዋሳን ጨምሮ በመላው ሀገሪቱ ተገንብተው ነገር ግን ሙሉ በሙሉ አገለግሎት መስጠት በማይችሉ ስቴዲየሞች ዙሪያ ትኩረት ሰጥቶ የሚመክር እና ኢትዮጵያን በፍጥነት አህጉራዊና አለምአቀፋዊ ውድድሮችን በድጋሜ ማስተናገድ ወደምትችልበት ደረጃ ለማምጣት ያለመ “ሀገር አቀፍ የስፖርት መሰረተ-ልማት ፎረም” በቀጣዮቹ ሁለት ሳምንታት ውስጥ እንደሚያካሄድ እንዲሁም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ንግግር በማድረግ ለችግሮቹ መፍትሔ ለማምጣት እንደሚሰራ አስታውቋል።

 

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *