በካሜሮን አስተናጋጅነት የሚካሄደው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ዛሬ ምሽት መካሄድ ይጀምራል።

የካፍ መስራች እና የሶስተኛው የአፍሪካ ዋንጫ አሸናፊ የሆነችው ሀገራችን ኢትዮጵያ ከዘጠኝ አመታት ቆይታ በኋላ በተመለሰችበት ውድድር ዛሬ ምሽት 04:00 ላይ ከኬፕ ቨርድ ጋር የመጀመሪያ ጨዋታዋን ታደርጋለች።

ከዚህ ጨዋታ አስቀድሞ በኢትዮጵያ ምድብ የሚገኙት አስተናጋጇ ካሜሩን እና ቡርኪናፋሶ ምሽት 01:00 ላይ የውድድሩን የመክፈቻ ጨዋታ የሚያከናውኑ ይሆናል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምሽት ላይ ለሚያከናውነው የውድድሩ የመጀመሪያ ጨዋታ የሚጠቀምበት አሰላለፍ የሚከተለውን ይመስላል።

ግብ ጠባቂ

22 ተክለማርያም ሻንቆ

ተከላካዮች

15 አስቻለው ታመነ
16 ያሬድ ባየህ
20 ረመዳን የሱፍ
2 ሱሌማን ሀሚድ

አማካዮች

8 አማኑኤል ዮሐንስ
3 መስኡድ መሀመድ
7 ሱራፌል ዳኛቸው

አጥቂዎች

11 አማኑኤል ገብረ ሚካኤል
10 አቡበከር ናስር
9 ጌታነህ ከበደ (አምበል)

ምንጭ: የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *