አትሌት ለተሰንበት ግደይ ምሽቱን በስፔን ቫሌንሺያ ስታዲዮ ዴል ቱሪያ ባደረገችው የክብረወሰን ውድድር ከዚህ ቀደም በሀገሯ ልጅ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ (14:11.15) ከ12 ዓመታት በፊት ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን አሻሽላለች።

የ2015 እና 2017 የወጣቶች የአለም አገር አቋራጭ ውድድር አሸናፊዋ እና የ10,000ሜ የአለም የብር ሜዳሊያ ባለቤቷ ለተሰንበት፡ ውድድሩን 14:06.62 በመግባት ነው የክብረወሰኑ ባለቤት ለመሆን የበቃችው።

የአትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ10,000ሜ የዓለም ክብረወሰን ተሰበረ

በተመሳሳይ ሁኔታ በተከናወነው ሌላኛው የክብረወሰን ውድድር ዩጋንዳዊዉ አትሌት ጆሽዋ ቼፕቴጊ 26:11.00 በመግባት ቀነኒሳ በቀለ 12፡17.53 በመሮጥ ለ15 ዓመታት ይዞት የቆየውን ክብረ ወሰን አሻሽሎታል።

የ24 ዓመቱ አትሌት ከአንድ ወር በፊት የቀነኒሳን የ5000ሜ ክብረወሰን የሰበረው ሲሆን የዛሬውን ጨምሮ ባለፉት ሁለት አመታት አራት የዓለም ክብረወሰኖችን ማስመዝገብ ችሏል።

የወደፊቱ የረጅም ርቀት አትሌቲክስ ንጉስ እንደሚሆን ኃይሌ ገብረስላሴን ጨምሮ በብዙዎች እየመሰከረለት የሚገኘው ጆሽዋ፡ በ5 እና 10ኪሜ የጎዳና ላይ ውድድሮችም የዓለም ክብረወሰን ባለቤት መሆኑ አይዘነጋም።

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ምንም እንኳን ለአመታት የቆዩት ሁለቱ ክብረወሰኖቹን በአጪር ጊዜ ልዩነት ውስጥ ቢያጣም፡ አሁንም የ5000ሜ የቤት ውስጥ ውድድር የርቀቱ የክብረወሰን ባለቤት ነው።

ማስታወሻ፡ ሁለቱም የጆሽዋ ቼፕቴጌ ክብረወሰኖች በአለም አትሌቲክስ አስፈላጊው ማጣራት ተደርጎ በይፋ እስኪጸድቁ ድረስ አሁንም በቀነኒሳ ስም ነው የሚገኙት።

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *