አዲስ አበባ – መስከረም 20/2013 ዓ.ም – ኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ክለብ እና ሀበሻ ቢራ አክሲዮን ማህበር ለአንድ አመት የሚዘልቅ የማልያ ላይ የስፖንሰርሺፕ ስምምነት ተፈራርሙ።

ዛሬ በጎልደን ቱሊፕ ሆቴል በተከናወነው የስምምነት የፊርማ ስነ ስርዓት ላይ ይፋ በተደረገው መረጃ መሰረት፡ ሀበሻ ቢራ ከሀምሌ 01/2012 ዓ.ም ጀምሮ ለቀጣዮቹ 12 ወራት ክለቡን ስፖንሰር ለማድረግ 28, 250,000.00 በካሽ እንዲሁም እንደ ክለቡ ውጤታማነት እየታዬ የሚጨመር 7,500,000.00 በድምሩ የ35.7 ሚሊዮን ብር ገንዘብ የሚከፍል ይሆናል።

ሁለቱ ተቋማት ረዘም ላለ ጊዜ አብረው የሰሩ መሆናቸውን በመግለጽ ለወደፊትም ቢሆን እንደ እስካሁኑ በየአመቱ ብቻ ሳይሆን ረዘም ላለ ጊዜ በሚቆይ ስምምነት ስር አብረው ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።

የስምምነቱ ዝርዝር ሁኔታ በክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ወልዴ እንደተገለጸው

– ቀጥታ ክፍያ – 18 ሚሊዮን ብር
– ለልዩልዩ ዝግጅቶች ድጋፍ – 2 ሚሊዮን ብር
– ለደጋፊዎች ማልያ ህትመት – 4.5 ሚሊዮን ብር
– የ2013 የቤተሰብ ሩጫን ለማዘጋጀት – 3.75 ሚሊዮን ብር
– ቡድኑ ቻምፒዮን ከሆነ – 2.7 ሚሊዮን ብር
– ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ካጠናቀቀ – 900 ሺህ ብር
– ለእያንዳንዱ ጨዋታ ለተጫዋቾች ማበረታቻ ከ6-8 ሺህ ብር

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *