አዲስ አበባ – ጳጉሜን 05/2012 ዓ.ም – የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድርን ለመምራት የተቋቋመው የፕሪሚየር ሊጉ ሸር ካምፓኒ፡ በ2013ዓ.ም በሀገራችን የሚካሄደውን የሊግ ውድድር በሬድዮ የቀጥታ ስርጭት ማስተላለፍ ለሚፈልጉ የሚዲያ ተቋማት ሊሸጥ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በመሆኑም የሊግ ካምፓኒው በቀጣይ የሚካሄደውን የፕሪሚየር ሊግ ውድድር በቀጥታ የሬድዮ ስርጭት ለማስተላለፍ የሚያስችለውን መብት፡ ህጋዊ ፍቃድ ላላቸው የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ የሚዲያ ተቋማት ለመሸጥ በሚቀጥለው ሳምንት ጨረታውን እንደሚያወጣ ለማወቅ ተችሏል፡፡

ሊግ ካምፓኒው ቀደም ሲል የሊግ ውድድሩን የቀጥታ የቴሌቭዥን ስርጭት እና የውድድር ስያሜ ሽያጭ ጨረታ አውጥቶ አሸናፊውን ለመለየት በሂደት ላይ መሆኑ ይታወቃል ፡፡

የሚያገኘው ገቢ የካምፓኒውን እና የተወዳደዳሪ ክለቦችን ፋይናንሻል አቅም ያሳድጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

መረጃው፡ የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ነው

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *