አዲስ አበባ – ጳጉሜን 01/2012 ዓ.ም – የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) አመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በመጪው ታህሳስ ወር 2013 ዓ.ም የመጀመሪያ ሳምንት በአዲስ አበባ እንደሚያካሂድ ታውቋል።

የካፍ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይህንን ውሳኔ የወሰነው፡ ኢትዮጵያ ባለፈው ግንቦት ወር ላይ ልታሰናዳው የነበረው 70ኛው የአለም አቀፉ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (ፊፋ) አመታዊ ጉባኤ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት መታጠፉን ተከትሎ ነው።

ትላንት ማምሻውን ከአንታናናሪቮ ወደ ካይሮ ሲያመሩ አዲስ አበባ ላይ አጭር የትራንዚት ቆይታ ያደረጉት የካፍ ፕሬዝዳንት አህመድ አህመድ፡ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ እና ዋና ጸሀፊው አቶ ባሕሩ ጥላሁን የኢትዮጵያን የጉባኤው አዘጋጅነት በተመለከተ ማረጋገጫ እንደሰጡም ለማወቅ ተችሏል።

በአፍሪካ ሕብረት አዳራሽ እንደሚከናወን በሚጠበቀው በዚህ አመታዊ ጉባኤ ላይ እንደ አለም አቀፉ የኮቪድ ወረርሽኝ ሁኔታ የሚወሰን ቢሆንም፡ ከሁሉም የኮንፌዴሬሽኑ አባላት፣ ከሚዲያ እና ልዩ ልዩ አለም አቀፍ ተቋማት የሚውጣጡ እስከ 250 እንግዶች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *