በተለይም ለልዩ ስፖርት

– ሱፐር ስፖርት እና ካናል ፕሉስን ጨምሮ ሌሎችም ይጠበቃሉ
– መስከረም 15/2013 ዓ.ም ጨረታው ይከፈታል

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሸር ካምፓኒ ከቀጣዩ የውድድር አመት ጀምሮ የውድድሩን የስያሜ እና የቴሌቪዥን ቀጥታ ስርጪት መብትን ሊሸጥ መሆኑ ታውቋል።

ካምፓኒው በዚህ ሂደት ለመሳተፍ ፍላጎቱ እና አቅሙ ያላቸው የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ተቋማት የጨረታውን ዝርዝር ሁኔታ በተመለከተ የፊታችን እሁድ ከሚታተመው ሪፖርተር ጋዜጣ ሙሉ መረጃውን እንደሚያገኙ የተቋሙ ስራ አስኪያጅ አቶ ክፍሌ ሰይፈ ለልዩ ስፖርት ገልጸዋል።

እንደ አቶ ክፍሌ ማብራሪያ ተቋማቸው ባለፉት ወራት ከስያሜ እና የቴሌቪዥን መብት ሽያጭ የሚገኘው ገቢ፡ በምን መልኩ ለክለቦቹ ይከፋፈላል የሚለውን ቀመር ለማውጣት ልዩልዩ አለምአቀፍ ተሞክሮዎችን በመመርመር ሁሉንም ሊያግባባ የሚችል የአሰራር ስርዓት መዘርጋቱን እና በቀጣይ ክለቦች ተወያይተው ሲያጸድቁት ወደ ስራ እንደሚገባ ይጠበቃል።

በጥናቱ መሠረት፡ ከቴሌቪዥን መብት ሽያጭ ከሚገኘው ገቢ 50% የሚሆነውን ለሁሉም ክለቦች እኩል፡ የተቀረውን 50% ደግሞ በአመቱ መጨረሻ ላይ ክለቦቹ በሚያስመዘግቡት ውጤት ተመስርቶ ለማከፋፈል፤ እንዲሁም ከሊግ ስያሜ ሽያጭ የሚገኘውን ደግሞ ለሁሉም ክለቦች እኩል ለማከፈል መታሰቡን ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው አካላት ለማወቅ ተችሏል።

መስከረም 15/2013 ዓ.ም እንደሚከፈት በሚጠበቀው የጨረታ ስነ ስርዓት ላይ ግዙፎቹ እና አለምአቀፎቹ ሚዲያዎችን ሱፐር ስፖርት እና ካናል ፕሉስን ጨምሮ ከሀገር ውስጥም በርካታ ተቋማት እንደሚሳተፉ የሚጠበቅ ሲሆን፡ የጨረታ ሂደቱን የሚመራ የባለሞያዎች ኮሚቴ የሚቋቋም መሆኑንም ለማረጋገጥ ተችሏል።

author image

About Haileegziabher Adhanom

Sports Writer & Managing Editor

You Might Also Like...

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *